ዜና

አሜሪካ በምሥራቅ አፍሪካ አሳሳቢ ላለቻቸው ችግሮች መፍትሔ የሚያፈላልጉ አዲስ ልዩ ልዑክ ሾመች

Views: 55

አሜሪካ፤ የትግራይ ግጭት እና የታላቁ የህዳሴ ግድብ ውዝግብን ጨምሮ በአፍሪካ ቀንድ አሳሳቢ ላለቻቸው ወቅታዊ ችግሮች መፍትሔ የማፈላለግ ኃላፊነት የተጣለባቸው አዲስ ልዩ ልዑክ ሾመች።

የ62 አመቱ ጄፍሪ ፌልትማን የአሜሪካ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ ልዑክ ሆነው በውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ አንቶኒ ብሊንከን መሾማቸውን ዛሬ አርብ ባወጡት መግለጫ አስታውቀዋል ሲል የዘገበው ኢትዮጵያ ኢንሳይደር ነው።

አዲሱ ልዩ መልዕክተኛ ከሚያተኩሩባቸው መካከል ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን “በተለይ አሳሳቢ” ያሏቸው “የትግራይ ግጭትን ጨምሮ በቅጡ ያልረጋ የኢትዮጵያ ሁኔታ፣ በኢትዮጵያ እና በሱዳን መካከል እየተባባሰ የመጣው ውጥረት እና የታላቁ የህዳሴ ግድብ ውዝግብ” ይገኙበታል።

ብሊንከን እንዳሉት “ሹመቱ እርስ በርስ ለተሳሰሩ የፖለቲካ፣ የጸጥታ እና የሰብዓዊ ቀውሶች መፍትሔ ለማበጀት የሚደረገውን ዓለም አቀፋዊ የዲፕሎማሲ ጥረት ለመምራት አስተዳደሩ ያለውን ቁርጠኝነት ያሳያል።”

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com