ዜና

‹‹ኢዜማ የህዝቡን ማህበራዊ ፍትህን ለማረጋገጥ ይሰራል››  ፕሮፌሰር ብርሀኑ ነጋ

Views: 56

የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) የህዝቡን ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ጥያቄዎችን በመመለስ ማህበራዊ ፍትህን ለማረጋገጥ እንደሚሠራ የፓርቲው መሪ ፕሮፌሰር ብርሀኑ ነጋ ገለጹ።

ፕሮፌሰሩ በስድስተኛው ጠቅላላ ምርጫ ዙሪያ ከአባላትና ደጋፊዎቻቸው ጋር ዛሬ በአርባምንጭ ከተማ ተወያይተዋል።

በውይይቱ ወቅት የሀገሪቱ ፖለቲካ በዘር ላይ የተመሰረተ በመሆኑ በማንነት ላይ ያነጣጠሩ ጥቃቶች በህዝቡ ላይ እንዲደርስ ምክንያት መሆኑን ነው የገለጸት።

የኢትዮጵያ ፖለቲካ ከዘርና ሃይኖማት መነጠል አለበት ያሉት ፕሮፌሰሩ ፓርቲያቸው የሚያራምደው የዜግነት ፖለቲካ የኢትዮጵያን ህዝብ አብሮነትና መቻቻልን የሚያጠናክር መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ፓርቲው በፌደራሊዝም ስርዓት ሙሉ በሙሉ እንደሚያምን አመልክተው ሆኖም ዜጎች በተወካይ ሳይሆን ቀጥታ የሚያስተዳድሯቸውን አካላት በመምረጥ የሚተዳደሩበት መሆን እንዳለበት ጠቁመዋል።

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com