በአዲስ አበባ በግንባታ ላይ ያለ ህንጻ ተደርምሶ የሶስት ሰዎች ህይወት አለፈ

Views: 53

በአዲስ አበባ ቂርቆስ ክፍለ ከተማ ካዛንቺስ አካባቢ በግንባታ ላይ የነበረ አንድ ህንፃ ተደርምሶ የሶስት ሰዎች ህይወት ማለፉ ተገለጸ።

በክፍለ ከተማው ወረዳ 8 ካዛንቺስ ጁፒተር ሆቴል ፊት ለፊት በግንባታ ላይ የነበረ ህንፃ በመደርመሱ የሶስት ሰዎች ህይወት ወዲያውኑ አልፏል።

የአዲስ አበባ አተማ የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን የኮሚኒኬሽን ቡድን መሪ አቶ ጉልላት ጌታነህ እንደገለጹት ከሟቾች በተጨማሪ በአደጋው ሶሰት ሰዎች ቀላል፣ አንድ ሰው ደግሞ ከባድ ጉዳት ደርሶባቸዋል።

አደጋው የተከሰተው ዛሬ ከጠዋቱ 5 ሰዓት አካባቢ ሲሆን፣ በግንባታ ላይ የነበረ አንድ ህንፃ በመደርመሱ መሆኑንም ተናግረዋል።

በወቅቱ ከአደጋው ሰዎችን ለመታደግ 35 የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች፣ 3 ከባድና 4 ቀላል ተሽከርካሪዎች እንዲሁም 3 አምቡላንሶች መሰማራታቸውን አቶ ጉልላት ገልጸዋል፡፡

በወቅቱ በቦታው ስራ ላይ የነበሩ 109 ሰዎችን ከአደጋው መታደግ ተችሏል ተብሏል።

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com