ዜና

“የጁንታው አባላት ከአገር ውጭ ለመውጣት ያደረጉት ጥረት ከሽፏል” ፡- ሌ/ጄኔራል ባጫ ደበሌ

Views: 63

የጁንታው አባላት ከአገር ውጭ ለመውጣት የሞከሩት ጥረትና የነበራቸው እቅድ በመከላከያ ሠራዊቱ መክሸፉን፣ የመከላከያ ሠራዊት የግንባታ ስራዎች ዋና አስተባባሪ ሌ/ጄኔራል ባጫ ደበሌ ተናገሩ።

ሌ/ጄኔራል ባጫ ደበሌ ይህን ያሉት ወቅታዊ ሀገራዊ ሁኔታ አስመልክቶ ዛሬ ጠዋት በሰጡት መግለጫ ነው።

ሌ/ጄነራል ባጫ ደበሌ እንደተናገሩት የጁንታው አባላት ወደ ሱዳን ለመውጣት ሙከራ አድርገው ነበር።

ይሁን እንጂ፣ መከላከያ ሠራዊት የጁንታውን አብዛኛውን አባላት በመደምሰስ እቅዳቸውን አክሽፏል ብለዋል።

በሰሜን ሸዋ ዞንና በኦሮሞ ብሄረሰብ አስተዳደር ዞን በዜጎች ላይ የተፈፀመው ጥቃት የኦሮሞና አማራ ብሄሮችን ህዝብ ለማጋጨት የሚሹ ኃይሎች የፈጸሙት መሆኑንም ጄኔራሉ ገልጸዋል።

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com