ዜና

በአፍሪቃ የኮሮና ክትባት አለመፋጠን የአፍሪቃ አየር መንገዶችን ሊጎዳ እንደሚችል ተገለጸ

Views: 47

በዓለም ላይ በርካታ አገራት የኮሮና ቫይረስ ክትባት ያልወሰዱ ዜጎች ወደ ሀገራቸው እንዳይገቡ በመከልከል ላይ ናቸው። በደቡብ አፍሪቃ እና በእንግሊዝ አዲስ የቫይረሱ ዝርያ ከተከሰተ በኋላ፣ በርካታ አገራት የጉዞ እገዳ አስተላልፈዋል።

ዓለም አቀፉ የአየር ትራንስፖርት ማህበር ዛሬ ባወጣው ሪፖርት ብዙ አገራት አዳዲስ የኮሮና ቫይረስ ዝርያን ለመከላከል የጉዞ እገዳ እያስተላለፉ መሆኑን ጠቅሷል፡፡

በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ተቀዛቅዞ የነበረው የዓለማችን አቪዬሽን ኢንዱስትሪ በያዝነው ዓመት ከ47 ቢሊዮን ዶላር በላይ ኪሳራ ሊደርስበት እንደሚችልም ማህበሩ ገልጿል።

አሁን ላይ በዓለማችን ሁሉም ሀገራት የኮሮና ቫይረስ ክትባት በመሰጠት ላይ ቢሆንም፣ የክትባት መጠኑ በአፍሪቃ አነስተኛ ነው ያለው ማህበሩ፣ አገራት ክትባቱን ያልወሰዱ መንገደኞች ወደ አገራቸው እንዳይገቡ እገዳ ማስተላለፋቸው የአፍሪቃ አየር መንገዶችን ይጎዳልም ብሏል።

በመሆኑም፣ የአፍሪቃ አገራት ዜጎቻቸውን በፍጥነት መከተብ ላይ ሊያተኩሩ ይገባል ሲል አስጠንቅቋል።

የአየር ትራንስፖርት በአፍሪካ ከ6 ሚሊዮን በላይ ዜጎች የስራ እድል የፈጠረ ሲሆን፣ የኢትዮጵያ፣ የታንዛኒያ እና ደቡብ አፍሪቃ አየር መንገዶች በአንጻራዊነት በዚህ ዘርፍ የስራ እድል ተጠቃሚ የሆኑ አገራት ናቸው።

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com