ዜና

ጠ/ሚ ዐቢይ ከጎረቤት አገራት መሪዎች ጋር ውጤታማ ውይይት ማድረጋቸውን ገለጹ

Views: 59
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከስድስት ጎረቤት አገራት መሪዎች ጋር ውጤታማ ውይይት ማድረጋቸውን ገለጹ።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት ከጂቡቲ፣ ኬንያ፣ ኡጋንዳ፣ ሶማሊያ፣ ኤርትራ እና ደቡብ ሱዳን መሪዎች ጋር ውጤታማ ውይይት ማድረጋቸውን አስታውቀዋል።
በውይይታቸውም በሁለትዮሽ እና ቀጠናዊ ጉዳዮች ላይ በጋራ ለመስራት መስማማታቸውን ጠቁመዋል።
ኢትዮጵያ ከጎረቤት አገራት ጋር ያላትን ግንኙነት ለማጠናከር ቅድሚያ እንደምትሰጥም ነው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ የገለጹት።
Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com