ዜና

የዓለም አቪዬሽን ኢንዱስትሪ በተያዘው ዓመት ከ47 ቢሊዮን ዶላር በላይ ኪሳራ እንደሚደርስበት ተገለጸ

Views: 58

ኢንዱትሰሪው ከባለፈው ዓመት ጋር ሲነጻጸር ግን የተሻለ ትርፍ አስመዝግቧል፤

  • የአቬሽን ኢንዱስትሪው ባለፈው ዓመት 126 ቢሊዮን በላይ ዶላር ኪሳራ ማስተናገዱ ተገልጿል፤

የአቬሽን ኢንዱስትሪው ባሳለፍነው ዓመት ከ126 ቢሊዮን በላይ ዶላር ኪሳራ አስተናግዶ ነበር። ለአቪዬሽን ኢንዱስትሪው ኪሳራ ዋነኛው ምክንያት ኮሮና ቫይረስ እነደሆነም ተገልጿል። ዓለም አቀፉ የዓየር ትራንስፖርት ማህበር የዘንድሮው 2021 የፈረንጆች ዓመታዊ የአቪዬሽን ኢንዱስተሪ እንቅስቃሴ ሪፖርቱ እንዳስታወቀው ዘንድሮም ይህ ዘርፍ ኪሳራ ማስመዝገቡ ይቀጥላል ብሏል።

ማህበሩ በሪፖርቱ ላይ እንደጠቀሰው የዓለማችን የአቪዬሽን ኢንዱሰተሪ 47.7 ቢሊዮን ዶላር ኪሳራ ያስመዘግባል ብሏል። የዓለማችን አቪዬሽን ኢንዱስተሪ በሳለፍነው ዓመት 126.4 ቢሊዮን ዶላር ኪሳራ አስመዝግቦ እንደነበር ገልጾ ለኪሳራው ዋነኛ ምክንያቱ ደግሞ የኮሮና ቫይረስ መስፋፋት ባስከተለው ጉዳት ምክንያት እንደሆነ አስቀምጧል።

የማህበሩ ዋና ዳይሬክተር ዊሊ ዋልሽ እንዳሉት ብዙ ሀገራት የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመግታት የጉዞ እገዳ በማስተላለፍ ላይ መሆናቸው እና አዳዲስ የቫይረስ ዝርያ በመገኘት ላይ መሆኑ የአቪዬሽን ኢንዱስትሪውን እየጎዳው ነው ብለዋል።

የአቪዬሸን ኢንዱስትሪ ከዓምናው ጋር ሲነጻጸር በዘንድሮው ዓመት መሻሻል ቢያሳይም ጉዳቱ ከፍተኛ መሆኑን የተናገሩት ዳይሬክተሩ ሀገራት የሀገር ውስጥ በረራዎች ላይ እገዳ ማስተላለፍ የለባቸውም ሲሉ አስጠንቅቀዋል።

ይህ ዘርፍ በዘንድሮው 458 ቢሊዮን ዶላር ገቢ እንደሚያስገኝ ይጠበቃል ያሉት ዳይሬክተሩ እድገቱ ባለፈው 2020 የፈረንጆች ዓመት ከተገኘው 372 ቢሊዮን ዶላር ገቢ ጋር ሲነጻጸር የ23 በመቶ እድገት ያስመዘግባልተብሏል።

የአቪዬሽን ዘርፉ ኮሮና ቫይረስ ከመከሰቱ በፊት ማለትም በፈረንጆች 2019 ዓመት 838 ቢሊዮን ዶላር ገቢ አስገኝቶ እንደነበርም ማህበሩ በሪፖርቱ ገልጿል።

ይሁንና የአውሮፕላን እቃ ጭነት አገልግሎት ባለፈው ዓመት ከፍተኛ እድገት ያስመዘገበ ሲሆን በተያዘው ዓመትም እስከ 13 በመቶ እድገት ሊያስመዘግብ ይችላል ተብሏል። የኮሮና ቫይረስ ከመከሰቱ በፊት በአውሮፕላን የሚጓዙ ሰዎች ቁጥር ከ4 ነጥብ 5 ቢሊዮን ባሳለፍነው የፈረንጆች 2020 ዓመት ወደ 1 ነጥብ 8 ቢሊዮን ሰዎች ዝቅ ሲል የተጓዦች ቁጥር በያዝነው ዓመት ወደ 2 ነጥብ 4 ቢሊዮን ከፍ ሊል እንደሚችል ማህበሩ ገልጿል።

መንግስታት አየር መንገዳቸውን ከክስረት ለመታደግ የመሰረተ ልማት ግንባታ፤ወጪ መጋራት እና ሌሎች የማሻሸያ እርምጃዎችን እንዲወስዱ ያስጠነቀቀው ማህበሩ ሀገራት ይሄንን ካላደረጉ ወደ ኢንዱስተሪው ዳግም ላይመለሱ እንደሚችሉም አስጠንቅቋል። የአቪዬሽን ኢንዱሰትሪ ከ88 ሚሊዮን በላይ ለሆኑ ዜጎች የስራ እድል የፈጠረ ሲሆን የ3.5 ትሪሊዮን ዶላር ገቢንም ያስገኛል።

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com