ዜና

በሚቀጥሉት ወራት ውስጥ ኮሮናን በቁጥጥር ስር ለማዋል የሚያስችል አቅም አለ-የዓለም ጤና ድርጅት

Views: 49
የዓለም ጤና ድርጅት ዳይሬክተሩ ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም “በተከታታይ እና በፍትሃዊነት ተግባራዊ የምናደርግ ከሆነ ይህንን ወረርሽኝ በወራት ውስጥ በቁጥጥር ስር ለማዋል የሚያስችሉ መሳሪያዎች አሉን”ም ብለዋል፡፡ ዋና ዳይሬክተሩ የአለም ሀብትን ፍትሀዊ በሆነ መንገድ መጋራት እንደሚገባም አሳስበዋል፡፡
አሁን ላይ በዓለም ዙሪያ ከ 25-59 የዕድሜ ክልል የሚገኙ ሰዎች በከፍተኛ መጠን የወረርሺኙ ሰለባ መሆናቸውንና መጠኑም “አስደንጋጭ” በሚባል ደረጃ የሚገለፅ መሆኑ ግን አልሸሸጉም ወና ዳይሬክተሩ፡፡
እንደ ሮይተርስ ዘገባ ከሆነ “አንድ ሚሊዮን ሞት ለመድረስ ዘጠኝ ወራት ፣ 2 ሚሊዮን ለመድረስ 4 ወራትን እንዲሁም 3 ሚሊዮን ለመድረስ 3 ወራትን ወስዷል” በማለትም የወረርሺኙ መስፋፋት ፍጥነት እንደአብነት አስረድቷል ዶ/ር ቴድሮስ አድሀኖም፡፡
ሆኖም የአለም ጤና ጥበቃ በየዕለቱ የሚያቀርበውን መግለጫን ከስዊድን በእንግድነት የተከታተሉት የዓለም የአየር ንብረት ለውጥ ተሟጋች ግሬታ ቱንበርግ ፤የበለፀጉ ሀገራት ታዳጊ ሀገራት ውስጥ ካሉናተጋላጭ ከሆኑት ቡድኖች ይልቅ ቀድመው ለራሳቸው ታዳጊ ዜጎች ክትባት መስጠታቸው ተገቢ ያልሆነና ሥነ ምግባር የጎደለው ነው ሲሉ ተችቷል፡፡
ቱንበርግ እንዳሉት ከሆነ ከፍተኛ ገቢ ካላቸው ሀገራት ውስጥ ከአራት ሰዎች መካከል አንዱ የCOVID-19 ክትባት የሚያገኝ ሲሆን፤ በድሀ ሀገራት ግን አንድ ሰው ክትባት የሚከተበው ከ 500 በላይ ሰዎች መካከል ነው፡፡
አሰራሩም ግልፅ የሆነ “የክትባት ብሔርተኝነት” የተንፀባረቀበት እንደሆነ ነው የአየር ንብረት ለውጥ ተሟጋች ግሬታ ቱንበርግ አንስተዋል፡፡
Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com