ዜና

የግልገል በለስ ከተማና አካባቢው ወደ ሰላማዊ እንቅስቃሴ እየተመለሰ መሆኑን የአካባቢው ነዋሪዎች ገለፁ

Views: 42

በመተከል ዞን የግልገል በለስ ከተማና አካባቢው ወደ ሰላማዊ እንቅስቃሴ እየተመለሰ መሆኑን የአካባቢው ነዋሪዎች ገለፁ።
የአካባቢው ነዋሪዎች ቀደም ሲል የፀጥታ ስጋትና መፈናቀል አሳስቧቸው ነበር ገልጸዋል፡፡
ሰሞኑን ግን አንፃራዊ ሰላም በመኖሩ የንግድ እንቅስቃሴ ጭምር መጀመራቸውን ነው የገለጹት ።
ነዋሪዎቹ ፣ የአካባቢውን ሰላምና ፀጥታ ወደ ነበረበት ለመመለስ የመከላከያ ሰራዊት ከሌሎች የፀጥታ ኃይሎች ጋር በመሆን እየሰራ ያለው ስራ የሚበረታታ መሆኑን ተናግረዋል።
የምዕራብ ዕዝ ሕብረት ዘመቻ ኃላፊ ተወካይና የኮማንድ ፖስቱ አባል ኮሎኔል ፋሲል ግዛው ÷ የቀጠናውን ሰላም አስተማማኝ ለማድረግ ሌት ተቀን እየተሰራ መሆኑን ጠቁመዋል።
እንደ ኮሎኔል ፋሲል ገለፃ በተፈጠረው አንፃራዊ ሰላም የተለያዩ ማህበረሰቦችና ነዋሪዎች በአንድ ስፍራ መገበያየት ጀምረዋል ፡፡
ይህ ሰላም እንዳይቀለበስ በትኩረት እየተሰራ መሆኑንም ተናግረዋል።
አያይ ዘውምታላቁ የኢትዮጵያ የህዳሴ ግድብ ያለ አንዳች የፀጥታ ችግር እንዲጠናቀቅም ማንኛውንም መስዋዕትነት ለመክፈል ዝግጁ ነን ማለታቸውን ከመከላከያ ሰራዊት የፌስ ቡክ ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com