ዜና

በፎኖተ ሰላም ከተማ አንድ ፖሊስ ሲገደል፣ አንድ የአማራ ክልል አድማ ብተና አባል ቆስሏል

Views: 71

የምዕራብ ጎጃም ዞን ፖሊስ፤ በፍኖተ ሰላም ከተማ አንድ የፖሊስ አባል መገደሉን እና አንድ የአማራ ክልል አድማ ብተና አባል መቁሰሉን ዛሬ ባሰራጨው መልዕክት ገልጿል።

ትላንት ከቀኑ ወደ 7:30 አካባቢ በወለጋ የሚኖሩ ወገኖቻችን እየተገደሉ እየተጨፈጨፉ ነው እየሞቱ ነው” በሚል ጉዳት ደረሰብን የሚሉ ህብረተሰቡን እና የአካባቢውን ወጣት በማስተባበር ተቃውሟቸውን በሰላማዊ ሰልፍ እንገልፃለን በማለት ወደ አደባባይ ወጥተው እንደነበር ተገልጿል።

ፖሊስ፣ “ሰልፈኞቹ ተቃውሟቸውን እየገለፁ በነበረበት ወቅት ሰላማዊ ተቃውም ወደ ሕገወጥ ነውጥ በማምራቱና በመሸጋገሩ በፍኖተ ሰላም ከተማ ፓሊስ እና የፀጥታ ኃይል የክልሉ አድማ ብተና ፓሊስ ሰላማዊ ሰልፍ ወደ ነውጥነት ባህሪ ሲያሳይ የፀጥታ ኃይሉ ነውጡን እያረጋጋ ባለበት ጊዜ የተለያየ ተልዕኮ ባነገቡ አካላት ከሰልፉ በስተጀርባ በመሆን ማህበረሰቡን በቅንነት በታማኝነት ሲያገለግል የነበረን የፍኖተ ሰላም ፓሊስ ላይ ጥይት በመተኮስ የገደሉ ሲሆን፣ አንድ የአድማ ብተና ፖሊስ አባል ላይም አቁስለዋል” ሲል ሁኔታውን አስረድቷል።

ከፍኖተ ሰላም ከተማ በመውጣት ከደብረማርቆስ ወደ ባህር ዳር ድንች ጭኖ ሲጓዝ በነበረ FSR የጭነት መኪና የተቃጠለ ሲሆን፣ በሹፌሩ ላይ ጉዳት እንደደረሰ ፖሊስ ገልጿል።

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com