ዜና

ኢትዮጵያና ፈረንሳይ የጋራ ጥቅማቸውን ማሳካት በሚችሉበት ስልት ላይ መከሩ

Views: 68

ኅዳር 18/ 2014 ኢትዮጵያና ፈረንሳይ የጋራ ጥቅማቸውን ማሳካት በሚችሉበት ስልት እና ሌሎች የልማት ትብብሮች ላይ ውጤታማ መሆን በሚችሉበት ዘዴ ላይ ተወያዩ፡፡
የትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ ሚኒስትር ዳግማዊት ሞገስ በኢትዮጵያ ከፈረንሳይ አምባሳደር ሬሚ ማቬሹ ጋር መወያየታቸውን ገልጸዋል።
በውይይታቸውም የሁለቱ አገራት የጋራ ጥቅም ላይ ያተኮረ ሲሆን የሰብዓዊ አቅርቦት ጭነት ላይ ቅልጥፍናን ማረጋገጥ በሚቻልበት ዘዴ ላይም መክረዋል፡፡
ኢትዮጵያና ፈረንሳይ በትራንስፖርት እና በአቅርቦት (ሎጅስቲክስ) ዘርፍ በተለይም የፓሪሱን ስምምነት መነሻ ያደረገውን ከብክለት ነፃ የሆነ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ትግበራ ላይ የሚኖራቸውን ትብብር ከፍ ወዳለ ደረጃ ለማሻገር ተስማምተናል ማለታቸውን ከሚኒስቴሩ የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com