ዜና

የአሜሪካ መንግሥትና ኤምባሲው ኢትዮጵያን በተመለከተ አሳፋሪ የሐሰት ወሬ ከማሰራጨት እንዲቆጠቡ መንግሥት አሳሰበ

Views: 65
የአሜሪካ መንግሥትና ኤምባሲው ኢትዮጵያን በተመለከተ አዲስ አበባ ተከባለች፣ የሽብር ጥቃት ሊፈጸም ነው፣ ወዘተ በሚል አሳፋሪ የሐሰት ወሬ እና የስም ማጥፋት ዘመቻ ከማሰራጨት እንዲቆጠቡ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት አሳስቧል፡፡
የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ከበደ ዴሲሳ በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳይ ላይ ዛሬ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡
አቶ ከበደ በመግለጫቸው የአሜሪካ መንግሥት “ይህን ካላደረጋችሁ የምሰጣችሁን እርዳታ አቋርጣለሁ!” በሚል ማስፈራሪያ በኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳይ እና ሉዓላዊነት ጣልቃ እየገባ ነው ያሉት ሚኒስትሩ ይህ ማስፈራሪያ ለኢትዮጵያ አይሰራም ብለዋል፡፡
ዳያስፖራው ወደ ሀገሩ የሚልከው የገንዘብ ድጋፍ ከእርዳታ የሚገኘውን እየተካ ነው ያሉት ሚኒስትር ዴኤታው ሀገርን ከኢኮኖሚ ጦርነት ለመታደግ የሚደረገው ርብርብ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጠይቀዋል፡፡
በኢትዮጵያውያ እና በዓለም ዙሪያ የሚኖሩ ዜጎች ድምጻቸውን ከፍ አድርገው ማሰማት መጀመራቸውን ተከትሎ ታዋቂ ግለሰቦችን ጨምሮ አፍሪካውያን ከኢትዮጵያ እውነት ጎን መቆም እና በሀገሪቱ ላይ እየተደረገ ያለውን ያልተገባ ጫና መቃወም መጀመራቸውን አንስተዋል፡፡
በርካታ የአፍሪካ፣ እስያ እና አውሮፓ ሀገራት ለኢትዮጵያ አጋርነት ማሳየታቸውን ጠቅሰው የኢትዮጵያ ጸረ ቅኝ አገዛዝ ትግል የአፍሪካና የመላ ጥቁር ህዝቦች ጭምር እየሆነ መሄዱን ተናግረዋል፡፡
በአሜሪካም ቢሆን ጥቂት የማይባሉ የህዝብ እንደራሴዎች፣ ታዋቂ ግለሰቦችና ዜጎች ከኢትዮጵያ ጎን መቆማቸውን የገለጹት ሚኒስትር ዴኤታው በተደረገባት ያልተገባ ጫና ምክንያት ሀገሪቱ በርካታ የክፉ ቀን ወዳጆችን ማፍራት መቻሏንም ጠቅሰዋል፡፡
Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com