ዜና

ከግድቡ ጥበቃ ጋር በተያያዘ አስፈላጊውን ግዳጅ እየተወጣ እንደሆነ መከላከያ አስታወቀ

Views: 59

በቅጥረኛ ተላላኪ ሃይሎች አማካኝነት ለተደረጉ ተደጋጋሚ ትንኮሳዎች “በሕዳሴው ዘቦች” ምላሽ መሰጠቱንም ነው ያስታወቀው

ከታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ጥበቃ ጋር በተያያዘ አስፈላጊውን ግዳጅ እየተወጣ እንደሆነ የሃገር መከላከያ ሰራዊት አስታወቀ፡፡

ሰራዊቱ በግድቡ ቀጣና አስተማማኝ ሰላምን የማስፈን ግዳጁን በጀግንነት እየፈፀመ እንደሚገኝ በማህበራዊ ገጹ ባወጣው ዘገባ አስታውቋል።

የፌዴራል ፖሊስ፣ የአማራ፣ የጋምቤላ፣ የሲዳማ ፣ የደቡብ ክልል እና የቤኒንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የፀጥታ አካላት ከጎኑ ተሰልፈው ሀገራዊ ተልኳቸውን “በጀግንነት” በመፈፀም ላይ እንደሚገኙም ነው ሰራዊቱ ያስታወቀው፡፡

“የሀገራችን ሕዝቦች አሻራ ያረፈበት የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ያለአንዳች የፀጥታ ችግር” ግንባታው እተከናወነ ይገኛልም ብሏል ሰራዊቱ ቀን ከሌት ግዳጁን በማከናወን ላይ መሆኑን በመጠቆም።

ጠላት ቀጣናውን ለማተራማመስ በቅጥረኛ ተላላኪ ሃይሎች አማካኝነት ተደጋጋሚ ትንኮሳዎችን ማድረጉን ያስታወሰም ሲሆን “በሕዳሴው ዘቦች አይቀጡ ቅጣት ተቀጥቶ ሽንፈቱን ተከናንቧል” ብሏል።

በአሁኑ ሰአት በቀጣናው የተሰማሩ የሰራዊቱ ክፍሎች፣ የሜካናይዝድ እና እግረኛ ክፍለጦሮች፣ የክልል የልዩ ሃይል አባላት በተጠቀቅ ሆነው ግዳጃቸውን በመፈፀም ላይ እንደሚገኙም አስታውቋል።Unit 10 በመባል የሚታወቀውን የግድቡን የመጀመርያውን ተርባይን የሚያንቀሳቅሰው የጄኔሬተር አካል (Rotar) የማስቀመጥ ስራ ባሳለፍነው ወርሃ መስከረም ላይ በስኬት መከናወኑ ይታወሳል፡፡

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com