ዜና

ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፋ መንግሥት ፀረ ፌደራሊዝም አለመሆኑን በተግባር እያሳየ ነው አሉ

Views: 61
ኅዳር 14/2014  የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፋ መሀመድ መንግሥት ፀረ ፌደራሊዝም አለመሆኑን በተግባር እያሳየ ነው አሉ፡፡
11ኛ ክልል ሆኖ ዛሬ የተደራጀውን የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ምስረታ በማስመልከት በፌስቡክ ገፃቸው ባሰፈሩት ‹‹የእንኳን ደስ አላችሁ!›› መልዕክት ለውጡ ከመጣ መጋቢት 2010 ወዲህ ይህ ሁለተኛው አዲስ ክልል መሆኑን አስታውሰዋል፡፡
ከዚህ ቀደም ሲዳማ 10ኛ ክልል ሆኖ መደራጀቱን ያስታወሱት ርዕሰ መስተዳድሩ ይህም ‹የፌደራሉ መንግሥት ፀረ ፌደራሊዝም ነው› በሚል የሚሰነዘርበትን ወቀሳና የሐሰት ትርክት ውድቅ የሚደርግ ነው ብለዋል፡፡
ላለፉት 30 ዓመታት ሥራ ላይ የዋለው የኢትዮጵያ ሕገ መንግሥት ሕገ መንግሥታዊ ስርዓትን በጠበቀ መልኩ አዳዲስ ክልሎች የሚደራጁበትን የሕግ አግባብ ቢደነግግም በአሸባሪው ሕወሓት 27 ዓመት የአገዛዝ ዘመን የክልልነት ጥያቄን ማንሳት ወንጀል ሆኖ ሲያሳስር ኖሯል፡፡
Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com