ዜና

“ጠቅላይ ሚኒስትሩ ወደ ግንባር አቅንተው እኔ ቤት የምቀመጥበት አንድም ምክንያት የለም”፦ ብርጋዴር ጀነራል ካሳዬ ጨመዳ

Views: 70
“ጠቅላይ ሚኒስትሩ ወደ ግንባር አቅንተው እኔ ቤት የምቀመጥበት አንድም ምክንያት የለም፣ ያለኝን የውትድርና ጥበብ ተጠቅሜ ጠላትን ድል ለማድረግ ዝግጁ ነኝ ” ሲሉ ብርጋዴር ጀነራል ካሳዬ ጨመዳ ገለጹ።
ብርጋዴር ጀነራል ካሳዬ ጨመዳ ወቅታዊ ጉዳይን አስመልክተው ከኢዜአ ጋር የሰልክ ቆይታ አድርገዋል።
የጠቅላይ ሚኒስትሩ ወደ ግንባር ማቅናት ግንባር ላይ እየተዋደቀ ለሚገኘው ሰራዊት ከፍተኛ መነሳሳትና የሞራል ሰንቅ ይሆነዋል ብለዋል።
ጀነራሉ አክለውም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህንን ውሳኔ መወሰናቸው ኢትዮጵያ በአጭር ጊዜ ውስጥ ጠላትን ድል ለማድረግ ያግዛታልም ብለዋል።
ሰራዊቱ መሪው ጎን ሆኖ ሲዋጋ እንዴት ድል ማድረግ እንዳለበት ያውቅበታል ሲሉም ጠቁመዋል።
“እኔም አንድ ልጄን ይዤ በማንኛውም ሰዓት መከላከያ በሚፈልገው ቦታ ለአገሬ መስዋዕትነት ለመክፍል ዝግጁ ነኝ” ብለዋል።
ግንባር በመሄድ ያለኝን ውትድርና ጥበብ ተጠቅሜ ጠላትን በመደምሰስ ኢትዮጵያን ለማዳን ተዘጋጅቻለው ሲሉም ተናግረዋል።
መላው የኢትዮጵያ ህዝብም የጠቅላይ ሚኒስትሩን አርዓያ በመከተል ወደ ግንባር ማቅናት ያለበት በመዝመት ሌላው ደግሞ በመደገፍ ለአገሩ አስፈላጊውን ሁሉ ማድረግ ይኖርበታልም ብለዋል።
በተለይም የቀድሞ ሰራዊት አባላት ለዚህ ጥሪ ግንባር ቀደም በመሆን ትናንት ለአገራቸው የከፈሉትን መስዋዕትነት ዛሬም መድገም አለባቸው ሲሉ ጥሪ አቅርብዋል።
“ኢትዮጵያ” የሚለውን የነጻነት ስም የማስጠበቅ የታሪክ አደራ አለብን! ከእንግዲህ እኔ መከላከያን በግንባር ሆኜ ለመምራት ከዛሬ ጀምሮ ወደ ትግሉ ሜዳ እዘምታለሁ። ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ መግለጻቸው ይታሰወሳል።
Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com