ዜና

ጠ/ሚ/ር ዐቢይ በሰብኣዊ መብት ጥሰት ምርመራ ሪፖርት ላይ ያወጡት መግለጫ

Views: 67
ጥቅምት 24/2014  ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የኢትዮጵያ ሰብኣዊ መብቶች ኮሚሽን እና የተባበሩት መንግሥታት የሰብኣዊ መብት ከፍተኛ ኮሚሽነር አሸባሪው የሕወሓት ቡድን በኢትዮጵያ በተለያዩ ክፍሎች የፈጸመው ጥቃት ላያ ያደረጉትን ጥናት ውጤት በመርህ ደረጃ እንደሚቀበሉ ገለጹ፡፡
የሁለቱ ኮሚሽኖች የጋራ ጥናት በትግራይ መንግሥት የዘር ማጥፋት ወንጀል አለመፈፀሙን ማረጋገጡንም በበጎው አንስተውታል፡፡
ሪፖርቱም ሆነ የኢትዮጵያ መንግሥት ረሃብና ፆታዊ ጥቃትን እንደጦርነት መሳሪያ አለመጠቀሙን ቢያረጋግጡም ጠላቶቻችን ግን ዛሬም እኛን በሀሰት ሊከሱ ያለእረፍት ያረሴራሉ ብለዋል፡፡
ሪፖርቱ መንግሥት ሆን ብሎ የትግራይ ሕዝብ ሰብኣዊ እርዳታ እንዳይደርሰው አስተጓጉሏል የሚለውን ክስ እውነት የሚያደርግ መረጃ ማግኘት አለመቻሉንም አሳውቋል፡፡
መንግሥት ሪፖርቱ ከሸፈነው ጊዜና ስፍራ አንፃር እንዲሁም አንዳንድ ድምዳሜዎች ላይ የማይስማማባቸው ጉዳዮች ቢኖሩም ተቋማቱ በአስቸጋሪ ሁኔታዎች ውስጥ ሆነው የሽብር ቡድኑን እውነተኛ ስዕል ለማሳየት ያደረጉትን ጥረት አበረታተዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ የጥምር ምርመራው ሪፖርት ላይ በኢትዮጵያ መንግሥት ላይ የተሰነዘሩ መሠረተ ቢስ ውንጀላዎችን አካቷል በሚል ማዘናቸውን በመገለጽም መንግሥት ምርራው ሙሉ ባይሆንም እንደሚቀበለው ገልጸዋል፡፡
በሪፖርቱ የማንስማማባቸው ጉዳዮች ቢኖሩም ሰነዱ እያደረግነው ላለው የጥቃ ሰለባዎችን የመድረስ፣ ተጠያቂነትን ለማስፈንና የመከላከያ እርምጃዎች የማውሰድ ጥት አጋዥ እንደሆነ እንወስደዋለን ብለዋል፡፡
በጦርነቱ ንጹሃን ሰብኣዊ ክብርና ነፃነታቸው መገፈፉ ልብ ሰባሪ መሆኑንም ጠቅላይ ሚኒስትሩ አንስተዋል፡፡
Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com