ዜና

“በጥቅምት 24 በትግራይ በግፍ የተገደሉት ወታደሮች ብቻ ሳይሆኑ ኢትዮጵያም በዕለቱ ተገላለች”

Views: 69
በጥቅምት 24 በትግራይ በግፍ የተገደሉት ወታደሮች ብቻ ሳይሆኑ ኢትዮጵያም በዕለቱ ተገላለች ሲሉ የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ ተናገሩ፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በህወሃት የሽብር ቡድን የሰሜን እዝ ከጀርባው የተዋጋበት ጥቅምት 24 ቀን አንደኛ አመት መታሰቢያ ስነስርኣት ላይ ባደረጉት ንግግር በጥቅምት 24 በትግራይ በግፍ የተገደሉት ወታደሮች ብቻ ሳይሆኑ ኢትዮጵያም በዕለቱ ተገላለች፤ የኢትዮጵያ ህዝቦችም በዕለቱ ተጨፍጭፈዋል ብለዋል፡፡
ኢትዮጵያን ብለው ቤታቸውን ሰፈራቸውን ጥለው ሀገራቸውን ከጥቃት ህዝባቸውን ከመከራ ሊታደጉ በሰሜን ዕዝ የተሰለፉ ወንድሞቻችን እራሳቸው አብልተው አልብሰው ወንድሞቻቸውንን በግፍ በጭካኔ ስውኛ ባልሆነ መንገድ የተጨፈጨፉበትን ዕለት ለማሰብ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
ዕኩይ ሃሳብን ይዘው ሀገራችንን ለማዋረድ ለመበተን ክብራችን ለማውረድ የተነሱትን ኃይሎች በእጅ የማንል መሆናችንና ኢትዮጵያ በመሰዋዕትነት የምትቀጥል ሀገር መሆኗን ዳግም ቃል ኪዳን የምንገባበት ዕለት ነው ብለዋል፡፡
የህወሃት የሽብር ቡድን በመከላከያ ሰራዊት የሰሜን ዕዝ ላይ ጥቃት የፈጸመበት ቀን “አልረሳውም! እኔም የኢትዮጵያ ሰራዊት ነኝ!” በሚል በልዩ ሁኔታ ታሰቦ ይውላል፡፡
Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com