ዜና

የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ በቅርቡ የተካሔደውን የኦነግ ጠቅላላ ጉባዔ “ተቀባይነት የለውም” አለ

Views: 76

አቶ አራርሶ ቢቂላ የሚመራው የኦነግ ክንፍ መጋቢት 4 ቀን 2013 ዓ.ም ጠቅላላ ጉባዔ በማካሔድ አዲስ የአመራር አባላትን መምረጡን መግለጹ ይታወሳል፡፡

በዚህ ጉባዔ፣ አቶ አራርሶ ቢቂላን ሊቀመንበር፣ አቶ ቀጄላ መርዳሳ እና አቶ ብርሃኑ ለማ ደግሞ ምክትል ሊቀመንበር ሆነው ተመርጠው ነበር፡፡

ሆኖም፣ ምርጫ ቦርድ ትላንት መጋቢት 19 ቀን 2013 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ፣ የተከናወነውን ጠቅላላ ጉባዔ ተቀባይነት የለውም ሲል አስታውቋል።

ውሳኔውን መሰረት በማድረግም በዚህ ጉባዔ የተመረጡትን አዲስ አመራሮች እንደ ኦነግ አመራሮች መቀበል እንደማይችልም ገልጿል።

ከዚህም በተጨማሪ በምርጫው ለመሳተፍ እና እጩዎችን ለማቅረብ ያቀረቡትን ጥያቄ፣ አሁን የተመረጠው አመራር ተቀባይነት ካለማግኘቱ ጋር ተያይዞ ቦርዱ ጥያቄውን ማየት እንደማያስፈልገው ነው ያስታወቀው፡፡

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com