ዜና

ከዛሬ ጀምሮ ማስክ የማያደርጉ ሰዎች ተጠያቂ እንደሚደረጉ ተገለፀ

Views: 64

ማንኛውም ሰው ከቤት ውጪ ያለ ማስክ መንቀሳቀስ እንዲሁም በእጅ መጨባበጥ የተከለከለ ነው፡፡

ከዛሬ ሰኞ መጋቢት 20 ቀን 2013 ዓ.ም ጀምሮ የኮሮናቫ ቫይረስ መከላከያዎችን የማይተገብሩ ግለሰቦች እና ተቋማት በወንጀል ተጠያቂ እንደሚደረጉ መንግስት አስታውቋል፡፡

የጤና ሚኒስቴር፣ የፌደራል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ እና የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን በጋራ በሰጡት መግለጫ፣ የኮቪድ 19 ስርጭት በከፍተኛ ሁኔታ መጨመሩን ተከትሎ መስከረም 25 ቀን 2013 ዓ.ም በወጣው በመመሪያ ቁጥር 30 የተቀመጡትን የክልከላ እርምጃዎች ተከታትሎ ማስፈፀም አስፈላጊ ሆኖ መገኘቱን አስታውቀዋል።

በዚህም መሰረት ከዛሬ ሰኞ መጋቢት 20 ቀን 2013 ዓ.ም ጀምሮ በመመረያው የተቀመጡ የክልከላ እርምጃዎችን ተግባራዊ ለማድረግ ይሰራል ብለዋል።

የተለያዩ ክልከላዎችና ግዴታዎችን በግለሰብና በተቋማት ላይ የጣለው መመሪያው በሁሉም የሀገሪቷ ክፍሎች የሚተገበር ሲሆን፣ መመሪያውን የሚተላለፍ አካል በወንጀል ተጠያቂ እንደሚሆንም ተገልጿል።

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com