ዜና

የመጀመሪያው የትራንስፖርት ኢንቨስትመንት ጉባዔ እየተካሄደ ይገኛል

Views: 286

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 15፣ 2013 የመጀመሪያው የትራንስፖርት ኢንቨስትመንት ጉባዔ እየተካሄደ ይገኛል፡፡
ጉባዔው በኢትዮጵያ ሲካሄድ በዓይነቱ የመጀመሪያው ሲሆን፤ የትራንስፖርት ሚኒስቴር ካዘጋጀው የ10 ዓመት መሪ ዕቅድ ጋር ተጣጥሞ የሚካሄድ ነው ተብሏል፡፡
በጉባዔው ላይ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ጨምሮ የትራንስፖርት ሚኒስትር ኃላፊዎችና ሌሎችም ተገኝተዋል፡፡
በመድረኩ 44 ያህል ፕሮጀክቶች በመንገድ ልማት፣ በመንገድ ትራንስፖርት፣ በሎጂስቲክስ፣ በባቡርና በአየር ትራንስፖርት መስኮች መንግስት ከግሉ ዘርፍ ጋር ሊጣመር በሚችልባቸው እድሎች ላይ ምክክር ይደረጋልም ተብሏል።
የትራንስፖርት ኢንቨስትመንት ጉባዔው ከመጋቢት ዛሬ እና ነገ ይካሄዳል፡፡

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com