ዜና

ምክር ቤቱ 11ኛ መደበኛ ስብሰባውን ጀምሯል

Views: 310

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 14፣ 2013 5ኛው የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት በሚያካሂደው 6ኛ ዓመት የስራ ዘመን 11ኛ መደበኛ ስብሰባውን ጀምሯል፡፡
በስብሰባው ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በ10 ዓመቱ የልማት ዕቅድና በወቅታዊ ሃገራዊ ጉዳዮች ላይ ከምክር ቤት አባላት ለሚቀርቡላቸው ጥያቄዎች ማብራሪያና ምላሽ ይሰጣሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡
በተጨማሪም ምክር ቤቱ የምክር ቤቱን 6ኛ ዓመት የስራ ዘመን 10ኛ መደበኛ ስብሰባ ቃለ ጉባኤ መርምሮ እንደሚያጸድቅ ከህዝብ ተወካዮች ምክር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com