ዜና

የአዲስአበባ ፖሊስ ሕዝቡ ከሀሰተኛ መረጃ ራሱን እንዲጠብቅ መከረ

Views: 76

በአንዳንድ ማህበራዊ ሚዲያዎች የህበረተሰቡን በጋራ አብሮ የመኖር እሴቶችን የሚያናጉ ሀሠተኛ መረጃዎች እየተሠራጨ ነው።
የሀገራችን ሠላም አንቅልፍ የሚነሳቸው ፀረ ሠላም ሀይሎች ብሄርን ከብሄር ለመጋጨት በአዲስ አበባ ብሄርን እና ሃይማኖትን መሠረት ያደረገ ጥቃት ሊፈፀም ነው የሚል ሀሠተኛ መረጃ እያሰራጩ ይገኛል።
በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ በተላለፈው ሃሰተኛ መረጃ የአዲስ አበባ ፖሊስን የደንብ ልብስ የለበሱ ነገር ግን የፖሊስ መታወቂያ የሌላቸው ጸጉረ ልውጥ ወጣቶች በየቤቱ እየዞሩ ብሔር እና ሃይማኖት በመመዝገብ ላይ ናቸው።
እነዚህ ከየት እንደመጡ የማይታወቁ ጸጉረ ልውጦች በተወሰኑ ብሔሮችን እና ሃይማኖቶችን ለይተው ለማጥቃት እየተንቃሰቀሱ ነወ የሚሉ እና በነዋሪው ላይ አሉታዊ ተፅእኖ የሚያሳድሩ ሃሰተኛ መረጃዎች በስፋት እየተሰራጩ መሆኑን ኮሚሽኑ ደርሶበታል፡፡
በፀረ ሠላም ሀይሎች አየተሠራጨ ያለው ሀሠተኛ መረጃ ህብረተሰብን ለማደናገጥ እና ለማሸበር እንዲሁም ብሔርን ከብሔር ለማጋጨት እንዲሁም በህብረተሰቡ ላይ የፀጥታ ስጋት ለመፍጠር ሆን ተብሎ ታቅዶና ታስቦ እየተሰራጫ ያለ ሀሰተኛ መረጃ ነው፡፡
በማህበራዊ ሚዲያ የተለቀቀው ሀሰተኛ መረጃ በስፋት የተሰራጨ በመሆኑ በሰዎች የእለት ከእለት እንቅስቃሴም ላይ አሉታዊ የስነ ልቦና ጫና እያሳደረ ነው፡፡
በመሆኑ ከተገቢው አካል መረጃ ሳይጠይቁና ሳያረጋግጡ ሀሰተኛ መረጃ የሚሰራጩ እንዲሁም መረጃን ተቀብለው የሚያናፈውሱ አካላት ከህገ-ወጥ ተግባራቸው እንዲቆጠቡ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አሳስቦ ከተማዋ ላይ ሰላም እንደሌለ በማስመሰል ሀሰተኛ መረጃ የሚያሰራጩ አካላት ላይ ክትትል በማድረግ ምርመራ በማጣራት በህግ እንዲጠየቁ የማድረግ ስራን እየሰራ መሆኑን ኮሚሽኑ ገልፆል፡፡
የአዲስ አበባ ፖሊስ

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com