ዜና

በኢትዮጵያ የመጀመሪያው የትራንስፖርት ኢንቨስትመንት ጉባኤ ሊካሄድ ነው

Views: 331

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 13 ፣ 2013 በኢትዮጵያ የመጀመሪያው የትራንስፖርት ኢንቨስትመንት ጉባኤ በኢትዮጵያ ይካሄዳል፡፡
ጉባኤው ከነገ በስቲያ እና ሃሙስ የሚካሄድ ሲሆን የትራንስፖርት ሚኒስትሯ ወይዘሮ ዳግማዊት ሞገስ እንደ ተቋም የተዘጋጀው የ10 አመት መሪ እቅድም ከዚሁ መርሃ ግብር ጋር የተጣጣመ መሆኑን ተናግረዋል።
መድረኩ የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱን ራዕይና ዕቅዶችን መሰረት በማድረግ የዘርፉ ተቋማት በሙሉ የሚሳተፉበት ይሆናል ተብሏል።
በመድረኩ 44 ያህል ፕሮጀክቶች በመንገድ ልማት፣ በመንገድ ትራንስፖርት፣ በሎጂስቲክስ፣ በባቡርና በአየር ትራንስፖርት መስኮች መንግስት ከግሉ ዘርፍ ጋር ሊጣመር በሚችልባቸው እድሎች ላይ ምክክር ይደረጋልም ነው የተባለው፡፡

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com