ዜና

“በኢትዮጵያ የሚካሄድ የትኛውም ዓይነት አሉታዊ ጉዳይ ያሳስበናል”- ሴናተር ክሪስ ኩንስ፣ የጆ ባይደን መልዕክተኛ

Views: 272

ከኢትዮጵያ መንግስት ባለስልጣናት ጋር እንዲመካከሩ በአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ወደ አዲስ አበባ የተላኩት ዴሞክራቱ ክሪስ ኩንስ ከምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ጋር ተወያዩ፡፡
ክሪስ ኩን እና ልዑካቸው በኢትዮጵያ ስላለው ወቅታዊ ሁኔታ በአቶ ደመቀ ገለጻ ተደርጎላቸዋል፡፡
ኢትዮጵያ በቀጠናው የአሜሪካ “ቁልፍ አጋር” መሆኗን ያነሱት ሴናተር ክሪስ ኩን በበኩላቸው “በሀገሪቱ የሚካሄድ ማንኛውም አይነት አሉታዊ ጉዳይ አሜሪካን ያሳስባታል” ብለዋል፡፡ ሴናተሩ በትግራይ ክልል እየተደረገ ያለው ሰብዓዊ ድጋፍ ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባልም ነው ያሉት፡፡ አሜሪካ በቅርቡ በትግራይ ለተፈጠረው ቀውስ ድጋፍ የሚሆን የ52 ሚልዮን ዶላር ለመለገስ ቃል መግባቷ የሚታወስ ነው፡፡

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com