ዜና

መከላከያ ሰራዊት ወደ አጣዬ እና አካባቢው እየገባ እንደሚገኝ ተገለጸ

Views: 476

በአጣዬ እና በአካባቢው የተቀሰቀሰው ግጭት አጎራባች ወደሆነው የሸዋሮቢት ከተማ እና አካባቢው የመዛመት ዐይነት ሁኔታ እየታየበት ነው ተባለ፡፡ በሸዋሮቢት ከትናንት ጀምሮ የተኩስ እሩምታዎች እየተሰሙ መሆኑን የከተማው ነዋሪዎች ለአል ዐይን አማርኛ ገልጸዋል፡፡
በዛሬ የኢቲቪ የምሳ ሰዓት ዜና እወጃ ላይ የስልክ ቃለ መጠይቅ ያደረጉት የአማራ ክልል የአስተዳደርና ጸጥታ ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊ አቶ ሲሳይ ዳምጤ ዛሬ በሸዋሮቢት፣ ሰንበቴ እና ማጀቴ አካባቢዎች ላይ የተኩስ ልውውጦች እንደነበሩ ገልጸዋል፡፡
በሁሉም የሰሜን ሸዋ እና የኦሮሞ ብሄረሰብ ዞን አካባቢዎች ሊባል ባይችልም ሁኔታው እየተባባሰ መምጣቱንም ነው አቶ ሲሳይ የተናገሩት፡፡ በሸዋሮቢት እና በሌሎች አካባቢዎች ተመሳሳይ ጥቃትን ለመፈጸም ትንኮሳዎች እንዳሉም ጠቁመዋል፡፡
አቶ ሲሳይ የክልሉ መንግስት ማገዝ አለበት በሚል ለፌዴራል መንግስት ባቀረበው ጥያቄ መሰረት የመከላከያ ሰራዊት ወደ አካባቢው እየገባ እንደሚገኝም ተናግረዋል፡፡  ህዝቡ ባልተገባና በተሳሳተ መንገድ ወደ ሁከትና ብጥብጡ እንዳይገባ ሊጠነቀቅ እንደሚገባም ኃላፊው አሳስበዋል፡፡

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com