ዜና

ኢሰመኮ በጂማ ዩኒቨርሲቲ ሁከት ፈጥራችኋል በሚል የታሰሩ ወጣቶች በፍርድ ቤት ነጻ ቢባሉም እስካሁን አለመፈታታቸውን ገለጸ

Views: 268

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) እንዳስታወቀው ከየካቲት 6 ቀን 2013 ዓ.ም. ጀምሮ በእስር ላይ የሚገኘውን የወጣት ሙሃመድ ዴክሲሶንና በሱ መዝገብ የተከሰሱትን ሁለት ሰዎችን የፍርድ ቤት ሂደት በቅርበት እየተከታተልኩ ነው ብሏል።ወጣቶቹ የታሰሩት በጂማ ዩኒርሲቲ ምርቃት ላይ ሁከት ፈጥራችኋል በሚል ተጠርጥረው ነው፡፡
የጅማ ከተማ ወረዳ ፍርድ ቤት መጋቢት 7 ቀን 2013 ዓ.ም. ተከሳሾቹን በነጻ አሰናብቶ ከእስር እንዲለቀቁ ቢወስንም አሁንም አሁንም በእስር ላይ ናቸው ብሏል ኮሚሽኑ። ስለሆነም ኮሚሽኑ እስረኞቹ በተሰጠው ትዕዛዝ መሰረት በአስቸኳይ ከእስር እንዲለቀቁ እየጠየቀ የፍርድ ቤቶች ትዕዛዝ እንዲከበር በድጋሜ አሳስቧል፡፡

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com