ዜና

ተመድ 2 ሚሊዬን ደቡብ ሱዳናውያንን ለመርዳት ከ1 ቢሊዬን ዶላር በላይ ገንዘብ ያስፈልገኛል አለ

Views: 240

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ኢትዮጵያን ጨምሮ በአምስት አገራት ለተጠለሉ ደቡብ ሱዳናዊያን 1 ነጥብ 2 ቢሊዮን ዶላር እንደሚያስፈልገው አስታወቀ።
እንደ ድርጅቱ መረጃ ከሆነ ከ2 ሚሊዮን በላይ የደቡብ ሱዳን ዜጎች በኢትዮጵያ፣ ዲሞክራቲክ ኮንጎ፣ ዩጋንዳ፣ ኬንያ እና ሱዳን ተጠልለው ይገኛሉ።
በፕሬዝዳንት ሳልቫኪር ማያርዲት እና ሪክ ማቻር (ዶ/ር) መካከል በተጀመረው አለመግባባት ምክንያት ወደ እርስ በርስ ጦርነት ሚሊዮኖችን ለስደት ሲዳርግ በመቶ ሺህ የሚቆጠሩ ዜጎችን ደግሞ ለሞት ዳርጓል።
የተሻለ ሰላም ፍለጋ ወደ ጎረቤት አገራት የተሰደዱት የሀገሬው ዜጎች ህይወታቸውን ከተለያዩ አገራት በሚገኝ እርዳታ በመምራት ላይ ናቸው።
የመንግስታቱ ድርጅት አሁን ላይ እንዳስታወቀው በአምስት ጎረቤት አገራት ተጠልለው ለሚገኙ ደቡብ ሱዳናዊያን ሰብዓዊ እርዳታ ለመስጠት 1 ነጥብ 2 ቢሊዮን ዶላር እንደሚያስፈልገው መግለጹን ሲጂቲኤን አፍሪካ ዘግቧል።
ወቅቱ የኮሮና ቫይረስ እና የአንበጣ መንጋ የተከሰተበት ወቅት በመሆኑ ለስደተኞቹ የሚያስፈልገውን ድጋፍ እንዳሻቀበው የገለጸው ድርጅቱ አገራት ድጋፍ እንዲያደርጉ ጥሪውን አቅርቧል።

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com