ዜና

ፕሬዚዳንት ሣህለ ወርቅ ዘዉዴ ከወለደች በኋላ አገር አቀፍ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና የወሰደችውን ተማሪ አነጋገሩ

Views: 387

መጋቢት 7 ቀን 2013ፕሬዚዳንት ሣህለ ወርቅ ዘዉዴ ከወለደች በኋላ አገር አቀፍ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና የወሰደችውን ተማሪ በስልክ አነጋገሩ።
ፕሬዚዳንቷ ለተማሪዋ ያላቸውን አድናቆትም ገልጸዋል።
የኢፌዴሪ ፕሬዝደንት ሣህለ ወርቅ ዘዉዴ የመጀመሪያ ልጇን ከወለደች በኋላ የሀገር አቀፍ የማትሪክ ፈተና ከተፈተነችው ተማሪ ጌጤ ናደውን ጋር በስልክ ተነጋግረዋል።
ፕሬዚዳንቷ በዚህ ወቅት ተማሪዋ ልጇን በወለደች ማግስት ለፈተና በመቅረብ ለትምህርቷ ያሳየችዉን ቁርጠኝነት አድንቀዉ፤ ትምህርት ለተሻለ ህይወት ዋና መሠረት መሆኑን መግለጻቸውን የፕሬዚዳንት ጽህፈት ቤት አስታውቋል።
ፕሬዚዳንት ሣህለ ወርቅ ባለፈዉ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ወቅት በተመሳሳይ ልጅ ወልደዉ ፈተናቸዉን የተፈተኑ ሴት ተማሪዎችን በብሔራዊ ቤተ መንግስት ጋብዘዉ ለትምህርታቸዉ ያሳዩትን ቁርጠኝነት እንዲቀጥሉ ማበረታታቸዉ ይታወሳል፡፡
በሚዛን አማን ከተማ ነዋሪ የሆነችው ተማሪ ጌጤ ናደው የካቲት 29 ቀን 2013 ዓ.ም እሁድ ማታ ወልዳ ሰኞ ጠዋት ለፈተና መቀመጧ ልዩ ክስተት ሆኖ መዘገቡ ይታወሳል።ተማሪ ጌጤ ከፈተናው በኋላ “ፈተናውን በጥሩ ሁኔታ ተፈትና እንደጨረሰችና ዓላማዋን ለማሳካት ማድረግ የሚገባትን ሁሉ ማድረግ ተገቢ ነው፣ ሁለቱም ለኔ መልካም እድሎች በመሆናቸው ማድረግ የሚገባኝን በማድረጌ ተደስቻለው ” ማለቷ ይታወሳል።

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com