ዜና

የቀድሞ ቦክሰኛው ማርቪን በ66 ዓመቱ በድንገት መሞቱ ተገለጸ

Views: 80

የቀድሞው የመካከለኛ ክብደት ቦክሰኛው አሜሪካዊው ማርቨለስ ማርቪን ሀግለር በመኖሪያ ቤቱ በድንገት ማረፉን ባለቤቱ በፌስቡክ ገጿ ይፋ አድርጋለች፡፡
እንደ ባለቤቱ ካይ ጉሬራ መረጃ ከሆነ የቀድሞው ቦክሰኛ በአሜሪካ ኒው ሀምፕሻየር በሚገኘው መኖሪያ ቤታቸው በ66 ዓመቱ ሳይጠበቅ ህይወቱ አልፏል።
ለባለ ግራ እጁ ቦክሰኛ ማርቪል ሞት ምክንያቱ እስካሁን አልታወቀም።
ማርቪን በተለይም እንደ ጎርጎሮሲያውያኑ ዘመን አቆጣጠር ከ1980-1987 ድረስ ታዋቂ የነበረ ሲሆን በርካታ ሽልማቶችን ተቀዳጅቷል።

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com