ዜና

ሙስጠፌ ክቡር ሥራ የሰራውን አከበሩ

Views: 97

በሚሰራበት ባጃጅ ውስጥ የተረሳን 300 ሺህ ብር ለባለቤቱ ለመለሰው ወጣት፣ የሶማሌ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ ሙህመድ ምስጋና አቀረቡ፡፡

ሰሞኑን በሚሰራበት ባጃጅ ውስጥ የተረሳን 300 ሺህ ብር ለባለቤቱ የመለሰውን ወጣት ጉሌድ ኢብራሂም እና ቤተሰቡን ነው ዛሬ በጽሕፈት ቤታቸው ጠርተው አቶ ሙስጠፌ ምስጋና ያቀረቡት።

የወጣት ጉሌድ ተግባር የክልሉን መልካም ስም ከፍ ያደረገና የመልካም ቤተሰብ ውጤት መሆኑን ማሳያ ነው ብለዋል።

ወጣት ጉሌድ ኢብራሂም ቤተሰቡን ለማገዝ ሲል የዩኒቨርስቲ ትምህርቱን አቋርጦ የነበረ ሲሆን፣ በባጃጅ ስራ ላይ በማሰማራት ለሰራው መልካም ተግባር፣ የመልካም ቤተሰብ አስተዳደግ ውጤት መሆኑን ምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ ተናግረዋል።

የክልሉ መንግስትም ለወጣቱ ቤተሰብ ተገቢውን እገዛ ለማድረግ ዝግጁ መሆኑን ጠቅሰው፤ ለወጣት ጉሌድም ያቋረጠውን ትምህርቱን እንዲያጠናቅቅና የስራ እድል እንዲሚፈጠርለት መንግስት ድጋፍ ያደርግለታል ማለታቸውን ከሶማሌ ክልል መገናኛ ብዙኃን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com