ዜና

የዘይቱን ቅጠል እና የዘይቱን ወለላ ለጤና

Views: 359

መግቢያ፡-

ዘይቱን (Psidium guajava ) ነቅ መገኛው ላቲን አሜሪካ ሲሆን፣ የፍራፍሬ ተክል ነው፡፡ የፍራፍሬው ዓይነት በዋናነት ወይም የተለመደው ቢጫ ወይም ነጣ ያለ ነው፡፡ ፍራፍሬው ምግብ እና መድኃኒት ይሆናል፡፡ ቅጠሉ መጠጥ እና መድኃኒት ይሆናል፡፡ ይህ በሌሎች አገራት ያለው ልዩ ጠቀሜታው ቢሆንም፣ በአገራችን ትኩረት አልተሰጠውም፡፡ ዛፉ በብዙ ሰዎች ጊቢ ውስጥ ይታያል፡፡ በአንዳንድ ቦታ ፍራፍሬው በሜዳ ላይ ወድቆ ይበሰብሳል፡፡ በአንድ ወቅት የዘይቱን ወለላ ተብሎ የፍራፍሬው ጭማቂ ለገበያ ይቀርብ ነበር፡፡ አሁን ግን ብዙም አይታይም፡፡

 1. የዘይቱን አጠቃቀም በቤት ውስጥ
 • የፍራፍሬው አጠቃቀም

የበሰለውን ፍራፍሬውን እንዲሁ አጥቦ መመገብ ይቻላል፡፡ ነገር ግን የተሻለ የሚሆነው በጁስ መሥሪያ ማሽን ውስጥ ጨምሮ መምታት፣ ዘሩን ማጥለል እና ጁሱን መጠጣት ነው፡፡ ይህ ጁስ የዘይቱን ወለላ ይባላል፡፡ የዘይቱን ወለላ ለልጆች እና አንጀታቸው ደካማ ለሆኑት በጣም ተፈላጊ ነው፡፡ ነገር ግን፣ ዘይቱን በውስጡ ከሚገኘው ዘር (ፍሬ) ጋር በአንድነት ፍሬውን ሳያኝኩት ስልቅጥ አድርጎ መመገብም ይበጃል፡፡ ማጣቀሻ አንድ

የጁሱ ዓይነት እንደ ፍራፍሬው ቀለም ይለያል፡፡ ከታች በምስሉ ላይ ያለው የቀይ ዓይነት እና ነጣ የሚለው የዘይቱና ዓይነት ነው፡፡

Courtesy to https://www.shutterstock.com/search/guava+juice

Courtesy to https://simpletasty.recipes/10-healthy-guava-juice-recipes/

 • የቅጠሉ አጠቃቀም
 • እርጥብ ቅጠሉን ወይም ቀድሞ ደርቆ የተዘጋጀውን ቅጠሉን አጥቦ መቀቀል ነው፡፡ ማጥለል እና እንደሻይ መጠጣት ነው፡፡ በማር፣ በመዓዛማ ቅጠል፣ በቅመም ወይም በስኳር ማጣጣም ይቻላል፡፡
 • እርጥብ ቅጠሉን ወይም ደረቅ ቅጠሉን በብዙ መጠን መቀቀል እና ማብረድ፤ማጥለል፡፡ ይህ ለሰው ቆዳ፣ የቆዳ ላይ ቁስል፣ ለራስ ቆዳ፣ መታጠብ ወይም በመቀባት መድኃኒት ይሆናል፡፡
 • ለእንስሳት ቆዳ የተቀቀለው ከነቅጠሉ እያጠቡበት ተባይ ለማስወገድ፣ እከክ ለማከም፣ ቁስል ለማዳን ይጠቅማል፡፡
 1. ዘይቱን ፍራፍሬው እና ቅጠሉ የጤና ጠቀሜታው

የቫይታሚን ሲ ይዘቱ ጥሩ ስለሆነ የጤና በረከቱ ብዙ ነው፡፡ እንዲሁም የውስጡ ዘር-ፍሬ ሲመገቡት ከፍተኛ አሠር አለው፡፡  ማጣቀሻ ሁለት

 • ዘይቱን ሲመገቡት ወይም ሲጠጡት፡-
 • የበሽታ መከላከል አቅም ያጎለብታል፣
 • ለልብ ጤንነት ጠቀሜታ አለው፤
 • ለሰውነት ቆዳ ጤንነት እና ውበት ይረዳል፤
 • የደም ስኳርን ያስተካክላል፣
 • የምግብ ሥልቀጣ ሥርዓትን ይረዳል፣
 • ነቀርሳ ሊያስከትል የሚችለውን ጉዳት ይፋለማል፣
 • የሰውነት ክብደትን ለማስተካከል ይረዳል፣
 • ጉንፋን ቶሎ እንዲሻል ያደርጋል፣
 • አሠሩ ለሆድ ድርቀት እጅግ ይረዳል፤
 • ጥሩ ያልሆነውን ኮልስትሮል ለመቆጣጠር ይጠቅማል፤
 • የፕሮስቴት ነቀርሳ አደጋን ይቀንሳል፣
 • የዘይቱን ቅጠል ውኃ ለውጪ አካል
 • ለእራስ ቆዳ ጤና ይረዳል፣ ፀጉር እንዲያድግ ያደርጋል፣
 • በሰውነት ላይ የቆዳ ቁስል ቶሎ እንዲድን ያግዛል፤
 • ለእንስሳት ቆዳ የተቀቀለው ከነቅጠሉ ሲያጥቡበት ተባይ ከቆዳቸው ላይ እንዲወገድ ያደርጋል፤ እከክ ለማከም፣ ቁስል ለማዳን ይጠቅማል፡፡
 1. ዘይቱን ሜዳ ላይ የተረሳ ጥሬ ሀብት

ዘይቱን እንዲህ ባለ ብዙ ጠቀሜታ ሆኖ ሳለ፤ በአግባብ ባለመሰብሰቡ፣ ወደ ገበያ ባለመቅረቡ ምክንያት ባክኖ ይቀራል፡፡ ከታች በምስሉ የሚታየው ከዛፉ ላይ ፍራፍሬው ወድቆ መሬት ላይ የደረቀውን ነው፡፡

ያለ ዋጋ የቀረው የዘይቱና ፍራፍሬ ምስል፤ ከጅማ አካባቢ የተገኘ ነው፡፡

 1. ማጠቃለያ፡-

ዘይቱን ብዙ የጤና ጠቀሜታ ያለው መሆኑን አስተውሉ፡፡ በጊቢአችሁ የሚገኘውን ቅጠሉን እንደ ሻይ ተጠቀሙ፡፡ ከጓሮ የሚቀለም ወይም ከገበያ የሚገዛውን ፍራፍሬ ተመገቡ ወይም  ጨምቃችሁ የዘይቱን ወለላ አዘጋጁበት፡፡ በአገራችን የሚገኘውን ቅጠል እና ፍራፍሬውን በማቀናበር ለከፍተኛ ጠቀሜታ ማዋል ይቻላል፡፡ ዘይቱና እንደባከነ አይቅርብን፡፡

ማጣቀሻ፡-

ማጣቀሻ አንድ፤   https://www.healthbenefitstimes.com/health-benefits-of-guava-seeds/

ማጣቀሻ ሁለት፤    https://www.healthline.com/nutrition/8-benefits-of-guavas

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com