ዜና

‹‹ሕግጋተ ሥልጣን›› መጽሐፍ ለገበያ ቀረበ

Views: 111

በአንጋፋው የራዲዮ ጋዜጠኛ ጌታሁን ንጋቱ የተተረጎመው ‹‹ሕግጋተ ሥልጣን›› መጽሐፍ ለንባብ ቀረበ፡፡

ጋዜጠኛ ጌታሁን የተረጎመው የአሜሪካዊው ደራሲ ሮበርት ግሪኔ 48 laws of power የተሰኘው መጽሐፍ ነው፡፡

መጽሐፉ 48 ሕግጋትን የያዘ ሲሆን፣ ከታሪክ- ሕግጋቱን በመተግበር የተሳካላቸውን እና ባለመተግበር ደግሞ የወደቁትን ያጣቅሳል፡፡

‹‹መሪነት ጉልበት መጠቀም ብቻ አይደለም፣ ጥበብ እንጂ፤›› የሚለው መርህ የመጽሐፉ ቁልፍ መልዕክት ሲሆን፣ ይህንኑ ከመጀመሪያ እስከ መጨረሻው እያብራራ ያመላክታል።
በተለይ፣ የእንግሊዝኛውን መጽሐፍ ማግኘት ላልቻሉ የጦር ሠራዊትና ፖሊስ አባላት ጥሩ መማሪያ ይሆናል ሲል ተርጓሚው ለኢትዮ-ኦንላይን ገልጿል።ይህ መጽሐፍ በየደረጃው ላሉ የህዝብ አስተዳዳሪዎችም በጣም ጠቃሚ ነው ሲል አስረድቷል።
መጽሐፉን ሜክሲኮ ደብረ ወርቅ ህንፃ ጋ የሚገኘው ሀሁ የመጽሐፍት መደብር ያሳተመው ሲሆን፣ 365 ገፆች አሉት፤ በ180 ብር ዋጋ ለገበያ ቀርቧል።

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com