ዜና

በወልድያና አካባቢዋ በ15 ቀናት ውስጥ 76 ሰዎች በእብድ ውሻ ተነከሱ

Views: 107

በወልድያ ከተማና አካባቢው በሁለት ሳምንት ጊዜ ውስጥ በእብድ ውሻ የተነከሱ 76 ሰዎች ለህክምና መምጣታቸውን የወልድያ ሆስፒታል አስታወቀ።

የሆስፒታሉ ሜዲካል ዳይሬክተር ዶክተር ሞገስ በርየ ለኢዜአ እንደገለፁት፤ በአካባቢው የእብድ ውሻ በሽታ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተስፋፋ መጥቷል።
በእብድ ውሻ ከተነከሱት መካከል ስድስቱ ህጻናት መሆናቸውን ገልጸው፤ ከአንድ ዓመት ህፃን እስከ 82 ዓመት አዛውንት መጎዳታቸውን ተናግረዋል።
ከአጠቃላይ ተጎጅዎች መካከል 68ቱ ከወልድያ ከተማ እንዲሁም 8ቱ ከሰሜን ወሎ ከአምስት ወረዳዎች የመጡ መሆናቸውን ተናግረዋል።
ከተጎጅዎቹ መካከል ለ21ዱ ህሙማን በሆስፒታሉ ህክምና እንደተሰጣቸ የገለጹት ዶክተር ሞገስ፤ በሆስፒታሉ ባለው የመድሃኒት አቅርቦት እጥረት ምክንያት ቀሪዎቹ ወደ ደሴ ሆስፒታል ተልከው ህክምና እንዲያገኙ መደረጉን አመልክተዋል።

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com