ዜና

‹‹በሚቀጥለው ወር ነሐሴ ውሃ አልሞላንም ማለት አንገታችንን ቆርጠን ጣልነው ማለት ነው›› – አምባሳደር ዲና ሙፍቲ

Views: 93

የአልጀዚራ ጋዜጠኛ ለአምባሳደር ዲና ሙፍቲ ‹‹ሱዳንና ግብፅ ስምምነት ላይ ሳንደርስ ኢትዮጵያ ውኃ መሙላት አትችልም እያሉ ነው? በዚህ ጉዳይ ላይ የኢትዮጵያ አቋም ምንድን ነው?›› ብሎ ላቀረበላቸው ጥያቄ የሰጡት መልስ ነው፡፡

‹‹የዓባይ ግድብ የኢትዮጵያውያን አንገት ነው፤ ከአንገት ቀጥሎ ጉሮሮ ነው ያለው። ጉሮሯችን ውሀ የሚቀበለው ከምላሳችን ነው። ምሳላችን ውሃ ማግኘት የሚችለው ከአፋችን ነው። የዓባይ ግድብም ለኢትዮጵያውያን እንዲህ ነው›› በማለት አምባሳደር ዲና ሙፍቲ የውኃ ሙሌቱን አስፈላጊነት አስረድተዋል።

በመቀጠልም፣ ‹‹በሚቀጥለው ወር ነሐሴ ውኃ አልሞላንም ማለት አንገታችንን ቆርጠን ጣልነው ማለት ነው። ማንም በአንገቱ እንደማይደራደር ሁሉ፤ ኢትዮጵያዊያንም በዓባይ ግድብ ጉዳይ ለደቂቃም ቢሆን አንደራደርም። ግድቡም ይሰራል፤ ውኃው ይሞላል፤ የኢትዮጵያ አቋም ይሄ ነው!›› ብለዋል፡፡

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com