ሕክምና በቤታችን በድጋሚ ለገበያ ቀረበ
በሀገር ባሕል እውቀት አቀንቃኝ ደራሲ በቀለች ቶላ የተዘጋጀው ‹‹ሕክምና በቤታችን›› መጽሐፍ በድጋሚ ታትሞ ለገበያ መቅረቡን ደራሲዋ ለኢትዮ-ኦንላይን ገልጻለች፡፡
መጽሐፉ ሲታተም ለ7ኛ ጊዜ ሲሆን፣ በተፈጥሮ መድኃኒት የቤት ውስጥ ባሕላዊ ሕክምና እውቀትን የሚያመላክት ነው፡፡
ደራሲዋ፣ ይህን መጽሐፍ ያነበበ ሰው፡-
• ‹‹ስለ ጤና፣ ስለ በሽታ በቀላሉ አይጨነቅም፡፡ ነገሮችን ከብዙ አንጻር ይመለከታል፡፡
• መክፈል የማይገባውን ዋጋ አይከፍልም፤
• ተገቢውን የሕክምና ዓይነት ይመርጣል፣
• መመገብ የሚገባውን እና የማይገባውን ለይቶ ይረዳል፤
• በቀላሉ በቤት ውስጥ እንዴት እራሱን ማከም እንደሚችል ይለያል፤
• ለየትኛው የሕክምና ዓይነት ዋጋ መክፈል እንደሚገባው ያውቃል፡፡›› በማለት ለኢትዮ-ኦንላይን ገልፃለች፡፡
መጽሐፉን፣ በመጽሐፍት መደብሮችና በአዝዋሪዎች እጅ ያገኙታል፡፡
ለእጽዋት፣ ለአዝዕርት እና ለሀገር በቀል እውቀት ከፍ ያለ አትኩሮት የምትሰጠው የግብርና ባለሟል ደራሲ በቀለች ቶላ፤ በኢትዮ-ኦንላይን ሚዲያ ላይ በተከታታይ የምርምር ሥራዎቿን በማቅረብ ላይ ትገኛለች፡፡