ዜና

የቻይና ፕሬዝደንት ሀገራቸው ሙሉ በሙሉ ከከፋ ድህነት መውጣቷን አስታወቁ

Views: 72

በቻይና ባለፉት 40 ዓመታት 770 ሚሊዮን ዜጎች ድህነትን ድል መንሳታቸውን የገለጹት ፕሬዝደንች ዢ፣ 1.4 ቢሊዮን ያህል ህዝብ ያላት ቻይና “በታሪክ ተመዝግቦ የሚቀመጥ” ሌላ “ተዓምር” ፈጥራለች ብለዋል፡፡

ባለፉት 8 ዓመታት በየዓመቱ በአማካይ ከ10 ሚሊዮን በላይ ሰዎች ከድህነት መላቀቃቸው ተገልጿል፡፡

በእነዚህ ስምንት ዓመታት ውስጥ አሁን ባለው መለኪያ ከድህነት ወለል በታች የሚኖሩት የመጨረሻው 98.99 ሚሊዮን የገጠር ነዋሪዎች ከድህነት ተላቀዋል ሲጂቲኤን እንደዘገበው፡፡

በድህነት ስር የነበሩ ሁሉም 832 ወረዳዎች እና 128,000 መንደሮች ከድህነት ዝርዝር ውስጥ ተሰርዘዋል፡፡

“ሀገሪቱ በድህነት ቅነሳ ‘የቻይና ምሳሌ’ በመፍጠር ለዓለም ድህነት ቅነሳም ትልቅ አስተዋጽኦ አበርክታለች፡፡” ሲሉም ነው ዢ የተናገሩት፡፡

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com