ዜና

የኢትዮጵያ ወዳጅ ኢሊዮ ባሮንቲኒ ማን ነበር?

Views: 476

መስፍን ታደሰ
(ፒ ኤች ዲ)

የኢትዮጵያን የቅርብና የሩቅ ታሪክ ከመደበኛ ሥራው ውጭ የሚከታተለው ፕሮፌሰር መስፍን ታደሰ፣ በዛሬው ጽሑፉ የየካቲት ማስታወሻ በሚል ርዕስ የጻፈውን ልኮልናል።

መልካምንባብ፡፡ 

እኛ ኢትዮጵያውያን ከሰላሳ ሺህ በላይ የሚሆኑ ኢትዮጵያውያን በፋሽስት የኢጣልያ ወታደሮች የተጨፈጨፉበትን ቀን፡- የካቲት ፲፪ን ለማስታወስ በየዓመቱ ስድስት ኪሎ ከሚገኘው አደባባይ ዙርያ በሚደረግ የአከባበር ስነሥርዓት ላይ እንሰበሰባለን። እኔም ከልጅነት ጊዜ ጀምሮ ከሰፈር ጓደኞቼ ጋር እዚያ ቦታ እገኝ ነበር። ይህ ታዲያ ፋሽስት ኢጣልያንን እያስታወስን የፋሺዝምን አስከፊ ባህርዮችን እንዳንረሳው፣ እንድናወግዘው ያደርገናል።

ለመሆኑ ፋሽዝምን የተቃወሙና የታገሉ ኢጣልያኖች ነበሩ ወይ? ተቃውሟቸውንስ እንዴት ገለጹ? በዚህ አጭር ጽሑፍ አንዱን እንመለከታለን። ኢሊዮ ባሮንቲኒ ይባል ነበር። ዓለም አቀፍ የነፃነት ዐርበኛና የመጀመሪያው የጣልያን ኮሚኒስት ፓርቲ መስራች አባል ነበር።

እንደኤ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ፲፰፻፺ (1890) ዓ.ም ተወለዶ፤ በ፲፱፻፶፩ (1951) ዓ.ም ደግሞ በድንገተኛ የመኪና አደጋ ሕይወቱ አለፈ። ውልደቱ እና እድገቱ ጣልያን አገር ሲሆን የደፈጣ ውጊያ ሥልጠና በቻይና ተከታትሎ ነበር። ሙሶሎኒን ወደ ሥልጣን መንበር ያመጣውን ቡድን ተቃውሞ ጣልያን ውስጥ በተደረገ ፀረ ፋሽስት ትግል የተካፈለም ነበር።

ኢሊዮ ባሮንቲኒ፣ እ.ኤ.አ በ፲፱፴፰ ወይም ፲፱፴፱ አእ፣ ጎጃም ውስጥ።

ጣልያን ኢትዮጵያን ስትወር ከሁለት ጓደኞቹ (አንቶን ኡማር እና ዶሚኒኮ ሮላ) ከሚባሉ ጋር ወደ ኢትዮጵያ፣ በካርቱም በኩል ጎጃም ገብቶ ከኢትዮጵያ ዐርበኞች ጋር አብሮ የፋሽስት ጣልያን ወታደሮችን ተዋግቷል።

ለኢትዮጵያውያን ዐርበኞች የደፈጣ ውጊያ ሥልጠና ሰጥቷል። በራሪ ጽሑፎችን በአማርኛና በጣልያንኛ ቋንቋ በማዘጋጀት በጣልያን ለተያዙ የኢትዮጵያ የከተማ ነዋሪዎች እና ለዐርበኞች፣ በያሉበት፣ እንዲደርስ ያደርግም ነበር።

ከእነዚያ ዐርበኞች አንዱ ጃጋማ ኬሎ ነበሩ። የግራዚያኒ ሰላዮች ይህንን ሲያውቁ ሦስቱን የጣልያን ዐርበኞች ማሳደድ ጀመሩ። እነርሱም ሸሽተው ወደ ነጻው ምድር ወደ ሱዳን ገቡ።

ከኢትዮጵያ ሌላ ኢሊዮ ባሮንቲኒ በቻይና የደፈጣ ተዋጊ፣ በስፓኝ ወዶ ዘማች፣ በፈረንሳይና በሃገሩ በጣልያን አጥባቂ ወይም አክራሪ የፖለቲካ ፓርቲን አቋም አራማጅ የነበር በመሆኑ ጣልያኖች የጣልያን ቼ ጉቬራ ይሉት ነበር።

ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት ፍጻሜ በኋላ የተባበሩት መንግሥታት ኃይሎች (Allied Forces) ጦር ጄኔራል፣ ሃሮልድ አሌክሳንደር፣ የብሮንዝ ሜዳሊያ ሲሸልመው የሶቭየት ሕብረት ደግሞ የቀይ ኮከብ ኒሻን ሰጥቶታል።

ከፊት ለፊት ቁጢጥ ያለው ኢሊዮ ባሮንቲኒ፣ የቆሙት ከግራ ወደ ቀኝ ከበደ (የመንግሥት ባለስልጣን)፣ ጊላ ጊዮርጊስ (ዲፕሎማት)፣ ጳውሎስ ጌታሁን ተሰማ (በስደት ለነበረው መንግሥት ተጠሪ)፣ ዐርበኛ (ስሙ አልተጠቀሰም)።

ባሮንቲኒ ካሰለጠናቸው ዐርበኞች በከፊል።

 

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com