ዜና

ሮማን ለቅመም እና ለጤና

Views: 363

መነሻ፡-    

የሮማን ዛፍ በአገራችን በብዙ ቦታ ተተክሎ ይገኛል፡፡ እንደተክሉ ብዛት በተለይም ፍራፍሬው በገበያ ላይ አልዋለም፡፡ ለቤት ፍጆታም ብዙ ቤተሰቦች አይጠቀሙትም፡፡  ጠቀሜታውን የተረዱት ወፎች ከቅርፊቱ ሥር የሚገኘውን የውስጡን ፍሬ ለዘመናት አጣጥመውታል፡፡ የዛፉን ጠቅላላ አካል የባሕል ሐኪሞች እንደ አግባቡ ለጠቀሜታ አውለውታል፡፡

በአማርኛ ሲጠራ ሩማን ወይም ሮማን ይሉታል፡፡  (English  ፖሜግራናቴ፤  Pomegranate;   Scientific name (ፑኒካ ግራናቱም Punica granatum L., Punicaceae)   ይባላል፡፡

ሩማን ለምግብ፣ ለመጠጥ፣ ለመድኃኒት፣ እንጨቱ ለተለያየ ጠቀሜታ ይውላል፡፡  ነቅ መገኛው ፐርሲያ (originated in Persia) ነው፡፡ ወደ ሜድትራንያን አገራት፣ አረብ፣ አፍጋኒስታን፣ ህንድ እና ቻይና በቶሎ ተስፋፍቷል፡፡ ነገር ግን በቻይና ልዩ ሙገሳ አግኝቶ የቻይና አፕል “Chinese apple,” ተሰኝቷል፡፡ በዚህ ላይ ይበለጥ አንብቡ፡1

https://www.google.com/search?q=pomegranate+originated&ie=utf-8&oe=utf-8&client=firefox-b-ab

ሀ/ ሮማን የጤና ጠቀሜታው፡-

የሮማን ሁሉም ክፍሎቹ፣ ለሰውም ለእንስሳትም ለብዙ በሽታ የተፈጥሮ መድኃኒት ነው፡፡

የሮማን ክፍሎች ሲባል የትኞቹ ናቸው?

የሮማን አበባ፣ የሮማን ዘንጐች፣ ቀንበጥ፣ ዘንግ፣ የፍራፍሬው የውስጡ ዘር፣ የፍራፍራው ቅርፊት፣ የሮማን ቅጠል፣  ሥር፣ የሥሩ ልጣጭ፣ ግንድ፣ የግንዱ ልጣጭ፣ እኒህ ሁሉ ለየብቻቸው ወይም ከሌሎች የመድኃኒት ተክሎች ጋር እየተቀየጡ የተፈጥሮ መድኃኒት ይዘጋጅበታል፡፡

ይህ በእርጥብነቱ፣ በለጋነቱ ወይም ደርቆ ተወቅጦ ወዘተ የተፈጥሮ መድኃኒት ሊሆን ይችላል፡፡

ለሰው መድኃኒትነቱ፣ ለደም ግፊት፣ ለልብ በሽታ፣ ለስኳር በሽታ፣ ለካንሰር፣ ለአንጀት ትላትል ማስወገጃ ወዘተ ይሆናል፡፡ ሕክምና በቤታችን መጽሐፍ ላይ እና በዚህ መረጃ መረብ ላይ  https://www.webmd.com/vitamins/ai/ingredientmono-392/pomegranate      ይበልጥ አንብቡ፡፡

ለቤት እንስሳት ሲባል፣ ለፈረስ፣ ለከብት፣ ለበግ፣ ለፍየል፣ ለውሻ፣ ለዶሮ፣ ለድመት ጭምር ነው፡፡

ለእንስሳት ለአንጀት ትላትል ማስወገጃ እና የውጪ አካልን ከበሽታ ለማከም ይረዳል፡፡

ሮማን በኢትዮጵያም ሆነ ተክሉ በሚበቅልበት አገራት ሲበዛ ሁለገብ የተፈጥሮ መድኃኒት ነው፡፡

ለ/ ሮማን ለቅመም

ከሮማን ፍራፍሬ ላይ የውስጡ ዘር ተለይቶ ይወጣል፣ ይደርቃል፣ ይፈጫል፡፡ ይህ በኢራን፣ ሜደትራኒያን ዙሪያ ባሉት አገራት፣ ዩ.ኤስ.አሜሪካ፣ በአፍጋኒስታን፣ ሩስያ፣ ህንድ፣ ቻይና እና ጃፓን የታወቀ ቅመም ነው፡፡

የደረቀው የሮማን የውስጡ ዘር

በቤት ውስጥ ዘሩን ለማድረቅ በፀሐይ ሙቀት ወይም በሌላ ማድረቂያ ዘዴ መቀጠም ይቻላል፡፡ በፀሐይ ለማድረቅ እስከ አንድ ሳምንት ይቆያል፡፡ ከደረቀ በኋላ በጠርሙስ ዕቃ ውስጥ በማሸግ እስከ አንድ አመት ማቆየት ይቻላል፡፡  በፈለጉት ጊዜ መፍጨት ነው፡፡

በሳላጣ፣ በጁስ፣ በመጠጥ፣ ወዘተ ላይ ሊጨመር ወይም ሊነሰነስ ይችላል፡፡ ይህ ልዩ የሆነ ጣዕም ይሰጣል፡፡ ሮማን በሚያፈራበት ወራት ለቅማችሁ እንደዚህ በማዘጋጀት ቅመሱት፡፡  

በሌሎች አገራት፣ ደረቁን ዘር ወይም ዱቄቱን ለመግዛት በህንድ ወይም መሐከለኛ ምስራቅ አገራት ግሮሰሪ ውስጥ ይገኛል፡፡ አናርዳና፡  anardana ብላችሁ ፈልጉት፡፡

ሐ/ የሮማን ጁስ

የውስጡ ፍሬ ግሩም ጁስ ይዘጋጅበታል፡፡ እርጥቡ የውስጥ ፍሬ ዘሩ፣ በጁስ ማሽን ደህና አድርጎ መፍጨት ነው፡፡ ካስፈለገ ውሃ ማከል፤ ሳይፈጭ የቀረ ቢኖር ማጥለል፡፡ ይህንን በሚፈልጉት ጣዕም ጋር መጠጣት ነው፡፡

This image is courtesy to    https://www.orissapost.com/

የሮማን ፍራፍሬ ጁስ ለጤና

  • ለስኳር ታማሚዎች ጥሩ ምግብ ነው፤
  • ክብደት መቀነስ ለሚፈልጉት ይበጃል፣
  • የደም ግፊት ይቀንሳል፣
  • የጡት ካንሰር እና ፕሮስቴት ካንሰርን ይፋለማል፤
  • የመገጣጠሚያ እና የቁርጥማት ህመም ይቀንሳል፣
  • የባክቴሪያ እና ፈንገስን ጉዳት ይቀንሳል፣

ለሌላም የጤና በረከት ይጠቅማል፡፡

መ/ ሮማን እንዴት ይለማል

  • የዘንጉን ቁርጥራጭ መትከል፤
  • ዘሩን መትከል፤
  • ከችግኝ ጣቢያ ገዝቶ መትከል ይቻላል፡፡

በደጋ እና በወይና ደጋ ሁሉም ቦታ ይበቅላል፡፡   መልካም ንባብ፡፡

 

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com