በአዲስ አበባ ከተማ 322 ባለቤት አልባ ቤቶች እና ህንፃዎች ተገኙ

Views: 72

በአዲስ አበባ ከተማ 322 ባለቤት አልባ ቤቶች እና ህንፃዎች መገኘታቸውን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ ገለጹ፡፡

ምክትል ከንቲባዋ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከመሬት ወረራ፣ ባለቤት አልባ ህንፃዎች፣ ከኮንዶሚኒየምና የቀበሌ ቤቶች ዙሪያ የተደረገ የማጣራት ውጤት ላይ መግለጫ እየሰጡ ነው፡፡

እንደ ኢብኮ ዘገባ በጥናቱ ግኝት መሰረት 1338 ሄክታር መሬት በሕገ ወጥ መልኩ መያዙን ምክትል ከንቲባዋ ተናግረዋል፡፡

ባለቤት የሌላቸው ቤቶችና ህንጻዎች በሚል የተለዩ 322 ቤቶች መገኘታቸውን የገለፁት ምክትል ከንቲባዋ፣ ከፊሎቹ የተጠናቀቁና ግንባታቸው ያላለቁ ህንጻዎች በግኙቱ መለየታቸውንም ገልጸዋል፡፡

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com