የቀዳማዊት እመቤት ጽሕፈት ቤት ያስገነባው 12ኛው ትምህርት ቤት ተመረቀ
የቀዳማዊት እመቤት ጽሕፈት ቤት በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ጉጂ ሱሮ ቡርጉዳ ወረዳ የገነባውን ኢፋ ሱሮ ቡርጉዳ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ቀዳማዊት እመቤት ወይዘሮ ዝናሽ ታያቸዉ በዛሬዉ እለት መርቀዋል፡፡
የትምህርት ቤቱ ግንባታ 20 ሚሊዮን ብር ወጪ የተደረገበት ሲሆን፣ በሁለት ፈረቃ 2 ሺህ 600 ተማሪዎችን የመቀበል አቅም እንዳለው ተገልጿል።
ጽሕፈት ቤቱ በዛሬው እለት ያስመረቀው ኢፋ ሱሮ ቡርጉዳ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ግንባታቸዉ ተጠናቀው ከተመረቁት 12ኛው ነው።
ቀሪዎቹ ትምህርት ቤቶች በዚህ አመት ግንባታቸው የተጠናቀቁ ትምህርት ቤቶችን በሁሉም ክልሎች ማስመረቁን እንደሚቀጥል ከጽህፈት ቤቱ የተገኘው መረጃ ያሳያል።