በሱዳን የአብዬ ግዛት ነዋሪዎች የኢትዮጵያ ወታደር አመሰገኑ

Views: 76

በአብዬ የ24ኛ ሞተራይዝድ ሰላም አስከባሪ ሻለቃ በሰፈረበት የግደጅ ቀጣና የሚገኙ ነዋሪዎች፣ ሠራዊቱ ባይኖር በሕይወት መኖር አንችልም ነበር ሲሉ ተናገሩ።

በዩኒስፋ የበላይ ጠባቂ እና ኃይል አዛዥ ሜጀር ጀነራል ከፍያለው አምዴ የተመራው የዩኒስፋ አመራር፣ ሁሉንም የ24ተኛ ሞተራይዝድ ሻለቃ ሻምበሎች ለሁለት ቀናት ተዘዋውረው በጎበኙበት ወቅት በየአካባቢው ከሚኖሩ ነዋሪዎቸ፣ጎሳመሪዎች እና አመራሮች ጋር ውይይት አካሂደዋል።

በዚሁ ውይይት ወቅት የአካባቢው ነዋሪዎች እንደገለፁት፣ ሠራዊቱ ከማህረሰቡ ጋር ጠንካራ ግንኙነት እንዳለው በመጠቆም፣ ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይል ሌት ከቀን የአካባቢውን በረሀማነት ተቋቁሞ እኛን ከየትኛውም ጥቃት በመከላከል በሕይወት እንድንኖር አስችሎናል ብለዋል።

ሜጀር ጀነራል ከፍያለው አምዴ በበኩላቸው፣ የአብዬን ሰላም ለማስቀጠልና የማህበረሰቡን ደህንነት ለመጠበቅ በትኩረት የመስራቱን ጥረት አጠናክረን እንቀጥልበታለን ብለዋል።

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com