ዶ/ር ሊያ የኮቪድ 19 ክትባትን ለ92 ሀገራት ተደራሽ ለማድረግ በአስተባባሪነት ተመረጡ

Views: 49

የጤና ሚኒስትር ዶ/ር ሊያ ታደሰ የኮቪድ 19 ክትባትን ተደራሽ ለማድረግ በሚሰራው ዓለም አቀፍ የንቅናቄ ቡድን ውስጥ በአስተባባሪነት ተመረጡ፡፡

የንቅናቄ ቡድኑ በዓለም አቀፉ የጤና ድርጅት እና የክትባት ትብብር የሚመራ ሲሆን፣ የኮሮና ቫረስ ክትባት ለሁሉም ሀገራት በፍትሀዊነት ተደራሽ እንዲሆን የሚሰራ ነው፡፡

በቡድኑ አስተባባሪ ሆነው የተመረጡት የኢፌዴሪ ጤና ሚኒስቴር ዶክተር ሊያ ታደሰ፣ የኢንዶኔዢያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሬትኖ ማርሱዲ እና የካናዳ የዓለም አቀፍ የልማት ሚኒስትር ካሪና ጉልድ ናቸው፡፡

ቡድኑ እንዳስታወቀው የቫረሱ ክትባት ዝቅተኛ እና መካከለኛ ገቢ ላላቸው 92 የዓለማችን ሀገራት ተደራሽ የሚሆን ነው፡፡

በቡድኑ በኩልም ክትባቱ ከለጋሽ ሀገራት በመሰብሰብ ለ92 ሀገራት በፍትሓዊነት የሚከፋፈል ይሆናል፡፡

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com