‹‹ህወሓት የአፋር ነፃ አውጪን በመጠቀም ወደ ጂቡቲ ለመሻገር የወጠነው እቅድ ከሽፏል››

Views: 52

ሕግን በማስከበር ዘመቻ ወቅት መከላከያ እና የአፋር ክልል በመቀናጀት ባደረጉት ስምሪት በጁንታው ላይ ድልን መቀዳጀት መቻላቸውን የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አወል ዐርባ ገለፁ፡፡

ህወሓት ለጥፋት ዓላማው ማስፈፀሚያ ከአንድ ዓመት በላይ ሲያሰለጥንና ሲያስታጥቀው የነበረውንና ራሱን የአፋር ነፃ አውጪ ብሎ የሚጠራውን ኡጉጉሙ፤ ወደ ሠላም፣ ድርድርና ልማት ማስገባት መቻሉን ተናግረዋል፡፡
በዚህም ጁንታው ኡጉጉሙን በመጠቀም ወደ ጂቡቲ ለመሻገር የወጠነው እቅድ ሊከሽፍበት ችሏል ብለዋል፡፡
የመከላከያ መረጃና የአፋር ክልል ይህንን ሴራ አስቀድመው በመረዳት በፍጥነት አካባቢውን ባይቆጣጠሩት ኑሮ፣ ኡጉጉሙን በመጠቀም የጁንታው አመራሮች በቀላሉ ወደ ጅቡቲ ማምለጥ ይችሉ እንደነበር ከመከላከያ ሰራዊት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com