ጅቡቲ የነበሩ 179 የትራንስ ኢትዮጵያ ከባድ ተሽከርካሪዎች ወደ ሀገር ቤት እንዲመለሱ ተደረገ

Views: 44

በጅቡቲ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ባደረገው ጥረት ህወሓት በሰሜን ዕዝ የመከላከያ ሰራዊት አባላት ላይ ጥቃት ከመፈፀሙ ጥቂት ቀናት በፊት የቀድሞ የትራንስ ኢትዮጵያ አመራሮች ከጅቡቲ ወደብ እቃዎችን ለማምጣት በሚል ወደ ጅቡቲ ወስደው እንዲቆሙ ያደረጉ 179 ከባድ ተሽከርካሪዎችን ወደ አገር እንዲመለሱ ለማድረግ የተሽከርካሪዎቹ የቁልፍ ርክክብ ተደርጓል።
አዲሱ የትራንስ ኢትዮጵያ ኩባንያ ተወካይ ከጅቡቲ የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስቴር የኩባንያው ንብረት የሆኑ 179 ከባድ ተሽከርካሪዎችን ቁልፎች ተረክበዋል።
የኢትዮጵያ የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ትራንስ ኢትዮጵያ ሽብርተኞችን በገንዘብ በመደገፍ፣ በሕገ ወጥ የገንዘብ ዝውውር፣ በመሳሪያ የታገዘ ዘረፋ እና ሌሎች ወንጀሎች በመጠርጠሩ ተሸከርካሪዎቹ እንዲመለሱ ትዕዛዝ ሰጥቶ እንደነበር ተገልጿል።
በፍርድ ቤት ትዕዛዝ እና በሚመለከታቸው የጅቡቲ የመንግስት አካላት ትብብር የጅቡቲ መንግሥት ቁልፎቹን ከአሽከርካሪዎቹ መረከብ መቻሉ ተገልጿል።
ወደ አገራቸው ለመመለስ ፈቃደኛ ከሆኑት 14 አሽከርካሪዎች በስተቀር ቀሪዎቹ በጅቡቲ የስደተኞች መጠለያ ጣቢያ እንደሚገኙ ተነግሯል።

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com