‹‹የልዩ ጣዕም ቡና በቀጥታ ለውጭ ገበያ በማቅረባችን የተሻለ ገቢ እያገኘን ነው››

Views: 42

በጌዴኦ ዞን የልዩ ጣዕም ቡና የሚያመርቱ አርሶ አደሮች ምርታቸውን በቀጥታ ለውጭ ገበያ በማቅረብ የተሻለ ገቢ እያገኙ መሆናቸውን አስታወቁ።

አርሶ አደሮቹ አንድ ኪሎ ቡና በአምስት እጥፍ የዋጋ ጭማሪ እየሸጡ መሆኑን ለኢዜአ ተናግረዋል።

በይርጋጨፌ ወረዳ ኢዲዶ ቀበሌ ነዋሪ አርሶ አደር አብርሃም አገዘ “መንግስት ያመቻቸልንን እድል በመጠቀም የምናመርተውን የልዩ ጣእም ቡና በቀጥታ ለውጭ ገበያ በማቅረብ የተሻለ ገቢ እያገኘን ነው” ብለዋል።

ከምርት ሽያጭ እያገኙ ያለው ገቢም ወደ ባላሃብትነት እያሻገራቸው መሆኑን አርሶ አደሩ ተናግረዋል።

ባለፈው ዓመት በስምንት ሄክታር ማሳ ላይ ካመረቱት ቡና በጥንቃቄ ያዘጋጁትን 10 ሺህ ኪሎ ግራም ለውጭ ገበያ በቀጥታ በመሸጥ 2 ነጥብ 5 ሚሊዮን ብር ገቢ ማግኘታቸውን ለአብነት ጠቅሰዋል ።

“በተያዘው የምርት ዘመን 11 ሺህ 600 ኪሎ ግራም ጥራቱን የጠበቀ ቡና በማዘጋጀት ከ4 ሚሊዮን ብር በላይ ለማግኝት እየሰራሁ ነው” ብለዋል።

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com