‹‹ምርጫው ያለምንም ችግር እንዲጠናቀቅ የጸጥታ መዋቅሩ ከወዲሁ ሊዘጋጅ ይገባል››

Views: 48

ስድስተኛው ሀገራዊና ክልላዊ ምርጫ በአፋር ክልል ያለምንም የጸጥታ ችግር እንዲጠናቀቅ በየደረጃው የሚገኘው የጸጥታ መዋቅር ከወዲሁ በመዘጋጀት በቅንጅት ሊሠራ እንደሚገባ ተመለከተ።

ስድስተኛው ሀገራዊና ክልላዊ ምርጫና የጸጥታ ኃይሉ ሚና ዙሪያ ከክልል እስከ ወረዳ መዋቅር የተውጣጡ የጸጥታ ኃይሎች የተሳተፉበት የውይይት መድረክ ዛሬ በሠመራ ከተማ ተካሄዷል።

በክልሉ ሠላምና ጸጥታ ቢሮ የጸጥታ ኃይልና ተቋማት አቅም ማጎልበት ዳይሬክተር አቶ ይማም እድሪስ በመድረኩ ባቀረቡት የመነሻ ጽሁፍ ላይ እንደገለጹት፤ በሀገሪቱ ብሎም በክልሉ የተጀመረው ለውጥ በውጤታማነት ለማስቀጠል መንግስት ቁርጠኛ ነው።

ሆኖም፣ አንዳንድ ጸረ-ሠላም ኃይሎች ምርጫውን ለማደናቀፍ በተለይም ወጣቶችን በማሳሳት የጥፋት ተልዕኮ ማስፈጸሚያቸው ለመጠቀም ከመሞከር ወደ ኋላ እንደማይሉ ካለፈው ተሞክሮ መውሰድ ይገባል ብለዋል።

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com