ዜና

‹‹ግብጽና ሱዳን የሶስትዮሽ ድርድሩን በማስተጓጎል ድርድሩን ከአፍሪካ ሕብረት የማውጣት ፍላጎት አላቸው››

Views: 117
  • ኢትዮጵያ ሱዳንን መታገሷ ከፍርሃት ሳይሆን፣ “የሌሎችን ኃይሎች የጨዋታ ካርድ ላለመምዘዝ ነው”

ግብጽና ሱዳን የታላቁ ህዳሴ ግድብ የሶስትዮሽ ድርድሩን በማስተጓጎል ከአፍሪካ ሕብረት ወደ ተባበሩት መንግስታት የፀጥታው ምክር ቤት የመውሰድ ፍላጎት እንዳላቸው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ገለጹ።

የህዳሴ ግድብ ግንባታን ለማስተጓጎል የሚጥሩ ኃይሎች ስለመኖራቸውም ጠቅሰዋል።›

አምባሳደር ዲና ሙፍቲ፤ በሀገሪቱ ወቅታዊ ፖለቲካ፣ ኢኮኖሚያዊና ሌሎች አበይት የዲፕሎማሲ ክንውኖችን አስመልክተው ሳምንታዊ መግለጫ ሰጥተዋል።

በመግለጫቸውም የሱዳን ወታደራዊ ኃይል ወደ ኢትዮጵያ ግዛት ዘልቆ በመግባት ሕገ ወጥ እንቅስቃሴ እያደረገ ስለመሆኑ አንስተዋል፡፡

የኢትዮጵያና ሱዳን ድንበር ከ100 ዓመት በፊት ከተደረገው የድንበር ስምምነት በኋላ በአውሮፓዊያኑ አቆጣጥር 1972 በሁለቱ አገሮች ዳግም ለማካለል የጋራ ኮሚቴዎች ተቋቁመው እንደነበር አስታውሰዋል።

በ1972ቱ ስምምነትም የድንበር ማካለል ስራው እልባት እስኪያገኝ ከ100 ዓመት በፊት በነበረው ድንበር እንዲቆዩ ስምምነት እንደነበርና ስምምነቱም በአፍሪካ ሕብረትና በመንግስታቱ ድርጅት ተቀምጧል ብለዋል።

ያም ሆኖ በሱዳን በኩል ከዓመታት በፊት የተደረሰውን ስምምንት በመጣስ ዓለም ቀፍ ሕግን የሚጥስ፣ ሁለቱን አገሮች የማይጠቅምና በሌሎች ኃይሎች የሚገፋ ሕገ ወጥ እንቅስቃሴ እንዳለ ገልጸዋል።

በተለያዩ ጊዜያት የተጀመሩ በጋራ ድንበር ኮሚሽን የድንበር ማካለል ስራዎች በመመለስ የሁለቱን አገራት የድንበር ችግር በሰላም መፍታት በኢትዮጵያ በኩል ቅድሚያ የሚሰጠው እርምጃ ነው ብለዋል።

የኢትዮጵያና ሱዳን ሕዝቦች የረጅም ታሪካዊ ግንኙነት እንዳላቸው ያነሱት አምባሳደር ዲና የጋራ ዕድገትና ተጠቃሚነት እንጂ ጦርነት እንደማይሹ ገልጸዋል።

ይሁን እንጂ፣ የሱዳን ጦር በተጠናከረ ሁኔታ ድንበር የመግፋት እንቅስቃሴ ላይ መሆኑን አብራርተዋል።

በዚህ ዙሪያ ኢትዮጵያ እስካሁን በትግስት የምትመለከተው ለሠላምና ዲፕሎማሲ ቅድሚያ የምትሰጥና ዓለም አቀፍ መርህን የምትከተል በመሆኗ ነው ብለዋል።

የሱዳን ጦር የኢትዮጵያን ድንበር ጥሶ በመግባት እያደረገ ያለውን ሕገ ወጥ እንቅሰቃሴ ኢትዮጵያ መታገሷ ከፍርሃት ሳይሆን “የሌሎችን ሃይሎች የጨዋታ ካርድ ላለመምዘዝ ነው” ብለዋል።

 

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com