ኤፍ ቢ አይ የታጠቁ የትራምፕ ደጋፊዎች የተቃውሞ ሰልፍ ሊያደርጉ ይችላሉ ሲል አስጠነቀቀ

Views: 45

የአሜሪካ የወንጀል ምርመራ ቢሮ (ኤፍ ቢ አይ) ታጣቂ የዶናልድ ትራምፕ ደጋፊዎች ጆ ባይደን ቃለ መሃላ ከመፈፀማቸው በፊት በመላ አሜሪካ የተቃውሞ ሰልፍ ሊያደርጉ ይችላሉ ሲል አስጠነቀቀ።

የታጠቁ ቡድኖች ከስምንት ቀን በኋላ ተመራጩ የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን በዓለ ሲመታቸውን ከማከናወናቸው በፊት ዋሽንግተንን ጨምሮ በ50ዎቹ የአሜሪካ ግዛቶች ለመሰባሰብ ማቀዳቸው ተነግሯል።

ታጣቂዎቹ ተቃውሞ ሰልፍ ሊያካሂዱ ይችላሉ የሚለው ጉዳይ የተሰማው ለጆ ባይደን በዓለ ሲመት የፀጥታው ሁኔታ እየተጠናከረ ባለበት ወቅት መሆኑን ቢቢሲ ዘግቧል።

ጆ ባይደን በትናንትናው ዕለት በካፒቶል ሂል በሚካሄደው የቃለ መሀላ ስነ ስርዓት ላይ ለመገኘት ስጋት እንደሌለባቸው ተናግረዋል።

ተመራጩ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን እና ምክትል ፕሬዚዳንት ካሚላ ሃሪስ በዶናልድ ትራምፕ ፅንፈኛ ደጋፊዎች በካፒቶል ሂል ሁከት ከተቀሰቀሰ ሁለት ሳምንት በኋላ ቃለ መሀላ ይፈፅማሉ ተብሎ እየተጠበቀ ነው።

የፀጥታ አካላትም በካፒቶል ሂል የነበረው አይነት የፀጥታ ችግር ሊከሰት አይችልም ሲሉ መግለፃቸው ተጠቅሷል።

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com