የቅራቅርንና የማይጸብሪን የጦር ግምባር በመምራት ድል ያደረጉት የኮሎኔል አለምነው ሞላ የቀብር ሥነ ሥርዓት ተፈጸመ

Views: 64

የቅራቅርንና የማይጸብሪን የጦር ግምባር በመምራት ድል ያደረጉት የ33ኛ ክፍለ ጦር ምክትል አዛዥ ኮሎኔል አለምነው ሞላ የቀብር ሥነ ሥርዓት ተፈጸመ።

በህይወት ታሪካቸው እንደተገለጸው የማይጸብሪን ግንባር በመምራትና አካባቢውን ከጁንታው ነፃ በማድረግ የሕግ ማስከበር ዘመቻው እንዲሳካ ኃላፊነታቸውን በጀግንነት የተወጡ የጦር መሪ ናቸው።

የውትድርና ህይወትን በ17 ዓመታቸው የጀመሩትና ለ36 ዓመታት በትግል የቆዩት ኮሎኔል አለምነው በ51 ዓመታቸው በሀገረ ሠላም የጁንታውን ቡድን በቁጥጥር ስር ለማዋል ከጠላት ጋር በተካሄደ ውጊያ ነው ህይወታቸው ያለፈው።

የቀብር ሥነ ሥርዓታቸውም በጀግንነት ባህልና በክብር በደቡብ ጎንደር ዞን በንፋስ መውጫ ከተማ በቅድስት ስላሴ ቤተክርስቲያን ጥር 3 ቀን 2013 ዓ.ም ተፈጽሟል።

የ5 ልጆች አባት የሆኑት ኮሎኔል አለምነው ደርግን በማስወገድ፣ በኢትዮ ኤርትራና በሠላም አስከባሪነት ዘመቻዎችና በተለያዩ የትግል ቦታዎች ጀግንነታቸውን ያሳዩ ፅኑ የጦር መሪ እንደነበሩ አብመድ ዘግቧል።

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com