ስዊድን የኢትዮጵያን ‹ሪፎርም› እንደምትደግፍ ገለጸች

Views: 41

የሠላም ሚኒስትር ወይዘሮ ሙፈሪሃት ካሚል በኢትዮጵያ ከስዊድን አምባሳደር ሃንስ ሄንሪክ ሉንድኪስት ጋር ተወያዩ።

ሚኒስትሯ የስዊድን መንግስት በኢትዮጵያ በትምህርት፣ ሴቶችና ህጻናት፣ ሰላም ግንባታ ዘርፎች እንዲሁም በአጠቃላይ የሪፎርም ጉዞ ላይ እያበረከተ ላለው ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል።

የስዊድኑ አምባሳደር በበኩላቸው ሃገራቸው የኢትዮጵያን ሪፎርም ስራዎች አጠናክራ መደገፏን እንደምትቀጥል ተናግረዋል።

ወይዘሮ ሙፈሪሃት ካሚል መንግስት በሰሜን የሀገሪቱ አካባቢ አስፈላጊው መረጋጋት እንዲፈጠር እና በመልሶ ማቋቋም ስራ ላይ ትኩረት አድርጎ እየሰራ መሆኑን አስረድተዋል።

በመጨረሻም ኢትዮጵያና ስዊድን ያላቸውን የሁለትዮሽ ትስስር አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ቃል ገብተዋል።

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com